ቻይና የኮሮና ቫይረስን ለማከም የተጠቀመችባቸውን የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ልትሰጥ ነው።
ቻይና የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዎቹን ሁለት የህመም ደረጃዎች ለማከም
የተጠቀመችባቸውን የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ በድጋፍ መልክ ልትሰጥ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር ከቻይና የባህል ሃኪሞችና ተመራማሪዎች ጋር ቫይረሱን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል፡፡
ቻይና የባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም ስኬታማ በሆነ መልኩ የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር የቻለችባቸው መንገዶችን ለኢትዮጵያ ለማጋራት ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
በተለይ የቫይረሱ ህመም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ለማከም የተጠቀመችባቸውን ሁለት የመድሃኒቶች ዓይነቶች ለኢትዮጵያ በድጎማ መልክ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
ረጅም እድሜ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ የባህል ህክምና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረትም በቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ እና በሙያም እደግፋለሁ ብላለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.) የኮሮናን ቫይረስ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ ሀገር ከተጀመሩ ስራዎች ጎንለጎን የቻይና ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህላዊ መድሃኒቶችም ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው ወደ ስራ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት እንዲሳካም የቻይናን ልምድ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች መባሉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል ፡፡
News and Updates
- The Geda Panel discussion held on the 4th anniversary of the Geda system recorded in the world heritage
- በአንኮበር ወረዳ በጎረቤላ ከተማ ተገንብቶ ለተመረቀው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየም የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶች ተበረከቱለት
- ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!
- ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡
- ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡
- የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሣው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- ስፖርት ለሰላም! በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
- ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
- የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም ሙዚየም በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡