የኢፌዲሪ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አመራሮች ከአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ጋር በከተማዋ በሚገኙ ሆቴሎች ድንገተኛ ጉብኝትና ፍተሻ አካሄዱ፡፡
ሆቴሎች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ምን አይነት ጥንቃቄ ያርጋሉ የሚለውን ለመፈተሽ ነው ጉብኝቱ የተካሄደው፡፡ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ከሰአት በኋላ በካዛንቺስ እና ቦሌ አካባቢ በሚገኙ ሆቴሎች በመንቀሳቀስ ነው ጉብኝቱ የተደረገው፡፡
በኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው የተመራው ቡድን የሆቴል ተገልጋዮችን አቀማመጥና ርቀት አጠባበቅ፤ የሆቴሎችን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አቅርቦት፤ በአንድ ስፍራ ላይ የሚከማቹ ሰዎችን ብዛት እና መሰል ጥንቃቄዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡ በዚህም አብዛኞቹ በጥሩ ጥንቃቄ ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ አልፎ አልፎ ግን ሰዎች ተቀራርበው የተቀመጡባቸውና የጥንቃቄ ቁሳቁስ የማይጠቀሙ ሰራተኞች ያሉባቸውን ሆቴሎች እንዲያስተካሉ መንገራቸውን ገልፀዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር፣ የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት፣ የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ብስራት ተገኝተው የነበረ ሲሆን ለመገናኛ ብዙሃንም ስለጉብኝቱ አላማና ተያያዥ ጉዳዮች አጭር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት በሃገራችን ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ብዛት 43 የደረሰ ሲሆን በዛሬው ዕለት የመጀመሪያዋ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሴት መመዝገባው ይታወቃል፡፡
News and Updates
- The Geda Panel discussion held on the 4th anniversary of the Geda system recorded in the world heritage
- በአንኮበር ወረዳ በጎረቤላ ከተማ ተገንብቶ ለተመረቀው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየም የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶች ተበረከቱለት
- ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!
- ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡
- ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡
- የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሣው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- ስፖርት ለሰላም! በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
- ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
- የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም ሙዚየም በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡