የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(UNESCO) ከአደጋ መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ወጣ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(UNESCO) ላለፉት 21 አመታት በአደጋ መዝገብ ውስጥ የቆየውን የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የአለም ቅርስ ኮሚቴ በፖላንድ ክራኮው ባደረገው ስብሰባ አደጋ ውስጥ ከሚገኙ የአለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ ተወሰነ፡፡
የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እ.ኤ.አ ከ1978 በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን የዩኔስኮ ገምጋሚ ቡድን እ.ኤ.አ በ1995 ፓርኩ ያለበትን ሁኔታ ለዩኔስኮ ሪፖርት በማቅረብ እ.ኤ.አ በ1996 በተካሄደው በ20ኛው የዩኔስኮ መደበኛ ስብሰባ ፓርኩ ያለበትን አደገኛ ሁኔታ በመመልከት በአደጋ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ብሄራዊ ፓርኩ በአደጋ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ ምክነያት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል በፓርኩ ክልል ውስጥ የሰዎች ሰፈራ መስፋፋት፤ ልቅ እርሻና ቅጦሽ፤በፓርኩ ውስጥ የሚያልፍ መንገድ መኖር፤ እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ የፓርኩ ወሰን ክልል እየጠበበ መምጣት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም ምክነያት በፓርኩ ውስጥ የሚገኙት የዱር እንስሳት ቁጥር በተለይም የዋልያና ቀይ ቀበሮ ቁጥር በከፍተኛ መጠን መመናመን ለችግሩ ዋና ዋና ምክነያት ሆነው ቆይተዋል፡፡
ይሁን እንጅ ችግሩን ለመፍታት የፌደራል መንግስትና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባደረጉት ርብርብ ፓርኩ ከአደጋ መዝገብ ውስጥ እንዲወጣ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በዚህም የፌደራል መንግስት በፓርኩ ውስጥ የሚኖሩ ህብረትሰብ ክፍሎችን ለማስወጣት የ 158 ሚሊዮን ብር ካሳ ክፍያ ከመሸፈኑም ባሻገር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለተነሽዎች ምትክ ቦታ በማዘጋጀት 40 ሚሊዮን ብር የሚገመት የከተማ ቦታ በመስጠትና ተነሽዎች ንብረታቸውን እንዲያጓጉዙ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ስራው ስኬታማ እንዲሆን አድርገዋል፡፤
ዩኔስኮ በአለም ቅርሶች የአደጋ መዝገብ ዝርዝር ውጥ ያሉትን ሀገራት በአለም አቀፍ ቅርስነት ያስመዘገቧቸው ቅርሶች አደጋ እንደተጋረጠባቸው በማወቅ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ያደርጋል። ከዚህ አኳያ የICUN የተልዕኮ ቡድን ወደ ሀገራችን በመምጣት ባለፈው ወር ባደረገው ግምገማ መነሻ ሪፖርቱን ለዩኔስኮ በማቅረቡ እ.አ.አ ጁላይ 4/2017 በፖላንድ በተካሄደው የአለም ቅርስ ኮሚቴ መደበኛ ጉባየ ላይ ጉዳዩ ሰፊ ውይይትና ክርክር ከተደረገበት በኋላ ፓርኩ ከዩኔስኮ የአደጋ መዝገብ እንዲወጣ ኮሚቴው ወስኗል
በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ እንደ ዋልያ እና ጭላዳ ዝንጀሮ ያሉ ብርቅዬ እንሰሳትን ጠብቆ በማቆየት ረገድም የሚደነቅ ስራ መሰራቱን ኮሚቴው ገልጿል።
News and Updates
- The Geda Panel discussion held on the 4th anniversary of the Geda system recorded in the world heritage
- በአንኮበር ወረዳ በጎረቤላ ከተማ ተገንብቶ ለተመረቀው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየም የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶች ተበረከቱለት
- ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!
- ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡
- ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡
- የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሣው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- ስፖርት ለሰላም! በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
- ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
- የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም ሙዚየም በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡