ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚል በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው PATWA-Award (Pacific Area Travel Writers Association-Award) አሸናፊ ሆነች።

ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚል በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው PATWA-Award (Pacific Area Travel Writers Association-Award) አሸናፊ ሆነች። በሌላ በኩል የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው በዚሁ የ PATWA ሽልማት ላይ ከሰሃራ በታች ምርጥ የቱሪዝም ሚንስትር ሽልማትን አሸንፈዋል። 
የፓትዋ ሽልማት በየአመቱ በጀርመን በሚካሄደው እና በአለማችን  በሆነው ITB (Internationale Tourismuse Börse-Berlin) የቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ የሚሰጥ የእውቅና ስነ-ስርዓት ነው።
በዘንድሮው የፓትዋ ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች አስራ ሶስት የአለም አገራት ያሸነፉ ሲሆን ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚለው ዘርፍ ነው በቀዳሚነት ያሸነፈችው። በተጨማሪም ዶ/ር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ አምስት የተለያዩ ሀገራት ሚንስትሮች በየዘርፋቸው አሸንፈዋል።
በዚህም የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር እንኳን ደስ ያለን እያለ በዘርፉ ገና ብዙ ስራዎች እንደሚጠብቁን ስለሚታወቅ ሽልማቱ ለስራ የሚያነሳሳን እንጅ የምንኩራራበት አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

News and Updates News and Updates