ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ሲደረግ የነበረው የቱሪዝም እና የባህልና የስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ትስስር መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
በባህል፣ በቱሪዝምና በስፖርት ዘርፎች ለሁለንተናዊ ለውጥ /Transformation/ ለማምጣት ዓላማ ያለውና ፈርጀብዙ የልማት ሀሳቦችን ያቀፈው የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ወጥ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለተጨማሪ ግብዓት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ከነሐሴ 11-13 ሲካሄድ የቆየው ምክክርና ውይይት ተጠናቋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ መክፈቻ ላይ የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን የመጣውን ለውጥ በመጠቀም በባህል፣ በቱሪዝምና በስፖርት ዘርፎች ያሉንን ዕምቅ ዕውቀቶች በማልማትና ገበያ በማስፋፋት ገቢ ማስገኘት አለብን ብለዋል፡፡ አክለውም መድረኩ ዕቅዶቻችንን ከፌዴራሉ ዕቅድ ጋር አናበን ለመሥራት የጋራ አረዳድ እንዲኖረንና ያስቀመጥናቸውን እቅዶች ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወን ማሳካት እንድንችል ነው ያሉ ሲሆን በመሪ ዕቅድ የዘርፉን ሁለንተናዊ ለውጥ/Transformation/ በማምጣት ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ተምሳሌትነት ለማሸጋገር የሚያስችለን ነው ብለዋል፡፡
ከመሪ የልማት ዕቅዱ ውስጥ የቀጣይ የ5 ዓመት እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በተጨማሪም የዕቅድ ትስስር እና ቅንጅታዊ ሥራዎች ገለፃ በቅደም ተከተል በጽሑፍ አቅራቢዎች ቀርቧል፡፡
የ10 ዓመትመሪ የልማት ዕቅድ (ከ2013-2022) በዋናነት ታሳቢ የሚያደርገው በ2022 ሶስቱን ዘርፎች በባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት አገልግሎትን በማላቅ ኢትዮጵያን ከቀዳሚ የአገር ብልፅግና መሠረቶች አንዱ የማድረግ ራዕይ የሰነቀ ነው፡፡ በተለይም ባህል ለሀገራዊ ልማትና ዕድገት አበርክቶው የላቀ እንዲሆን ታሳቢ ማድረጉ፣ በቱሪዝሙ ዘርፍ ተወዳዳሪ ቱሪዝም እንዲኖረው ለየት ባለመልኩ በሀገሪቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚለሙ 59ኝ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት ፕሮጀክቶች (ለአብነት ጎረጎራ፤ ሃሮወንጪ፣ ኮይሻ /ዳውሮ/ … ወዘተ) መቀየሳቸው እንዲሁም ለ6 ሚሊዮን በላይ ሴቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ መሆኑ ለዜጎች ተስፋ ሰጪ ያደርገዋል፡፡
በመጨረሻም መርሀ ግብሩን ያጠቃለሉት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ በውይይቱ የተገኘውን ግብዓት ወስደን በማስተካከልና በማጠናቀር ወጥ እቅድ ሆኖ እንዲወጣ በማድረግ በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖር ሌላ መርሐ-ግብር እነደሚጸድቅ አቅጣጫ በማስቀመጥና የችግኝ ተከላ በማካሄድ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
News and Updates
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡