የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።

በወርሀ ጥቅምት ጎብኝዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ የምትገኘው ሀገራችን ጎብኝዎች ወደ ሀገራችን በሚመጡበት ወቅት ባለሙያቹ ማድረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች በተመለከተ በሀገራችን ለሚገኙ ሼፎች በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ስልጠና ተካሂዷል ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ በሀገራችን የቱሪዝም ማገገሚያ ስትራቴጂ የተቀመጡት ዋና ዋና ነጥቦች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ ተናግረው የዚህ መርሀ ግብር አንዱ የሆነው የቱሪዝም ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ መስጫ መድረኮች ባለፈው ወር በሀረሪ ክልል የተካሄደ ሲሆን ይህ የሼፎች ስልጠና የዚሁ መርሀ ግብር አንዱ አካል ነው ብለዋል።
ወደ ሀገራችን የሚመጡት ቱሪስቶች በርካታ ጊዚያቸውን በሆቴል ነው የሚያሳልፉት ያሉት አቶ ስለሺ በምግብ ማብሰያ አካባቢ በርካታ የጥንቃቄና ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ስለሚጠብቀን ይህንን ለማስተካካል ይህ ስልጠና ግብዓት እንደሚሆን ተናግረው በቀጣይም በአክሱም፣ በላሊበላ እና በባህርዳር እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

News and Updates News and Updates