የላልይበላ አብያተ-ክርስቲያናት ጥገናን በተመለከተ ትኩረት ሰጥቶ ለማስፈፀም የሚረዳ ጉብኝትና ውይይት ተካሄደ።

 

ብርት / ፎዚያ አሚን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር የቅዱስ ላልይበላን ውቅር አብያተ ክርስትያናት ጠግኖ ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግ የተጀማመሩ ስራወችን ለመመልከትና ትኩረት ሰጥቶ ለመምራት የሚረዳ ጉብኝትና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረጉ።

 

 

በጉብኝቱ የችግሩ ስፋት፣ እስካሁን የተጠገኑ የቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል እንዲሁም አሁን በጥገና ላይ ያለውን የጎልጎታ ሚካኤል ቤተክርስትያንን ተመልክተዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከከት ረዳት ጳጳስ እና የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪን ጨመሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ ወቅት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አቶ ዮናስ ደስታ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት የገለጹ ሲሆን የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቅርሶቹ ጥገና እንደሚያስፈልጋቸው ለጊዜው የተሰሩት መጠለያዎች መነሳት ይገባቸዋል የሚል መሆኑን፤ የጥገናወቹን አስተማማኝነት እንዲሁም የመጠለያዎቹን አነሳስ በተመለከተ ከዩኔስኮና መጠለያውን ከሰራው ኩባንያ የመጡ ባለሙያወች በቦታው ተገኝተው መመልከታቸውን፣ ከዩኔስኮ የጥገና አካሄድና መርሃ ግብር እንዲሁም የመጠለያውን አነሳስ ሂደትና ፕላን ግብረመልስ ሲቀርብ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልፀዋል። በተጨማሪም ከአጥር ከአብነት /ቤትና ከጽ/ቤት ግንባታ ጋር ተያይዞ የቅርስ ቦታ ላይ ሊገነባ በሚገባው ስታንዳርድ አግባብ መገንባት እንደሚቻል ግልጽ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ክብርት ሚንስትሯ የችግሩን ሁኔታ በደንብ መረዳታቸውን ገልጸው በቀጣይ በሚቀርቡ ሪፖርቶች መሰረት አስፈላጊውን አቅጣጫ አስቀምጠን ችግሩን ለመፍታት ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከክልል ከዞንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርብ በመሆንና በጋራ ሌት ከቀን እንሰራለን ብለዋል። ከዚህ ባሻገር አካባቢውን የማልማትና የማጽዳት ስራም ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሀገር ልማትና እድገት እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት በጋራና በልዩ ትኩረት መስራት ይገባናል ብለዋል። ክብርት ሚኒስትሯ ቦታውን በማየቴ በቀጣይ ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ድንቅ ቦታ መሆኑን ከመረዳትም ባሻገር ለቀጣይ እቅድ ግብአት ሊሆነን እንደሚችልና ብዙ መስራት እንደሚገባን ተረድቻለሁ አብረን እንሰራለን ብለዋል። በመጨረሻም የቅርሱን ጥገናና የመጠለያ ማንሳት ሂደት በተመለከተ በተጠና፣ ግልጽነትና አሳታፊነትን በመከተል የቅርሶቹን ደህንነት አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ በመስራት ጊዜያዊ መጠለያዎችን የማንሳት ተግባራት በቅንጅት ማከናወኑ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡


News and Updates News and Updates