ሀገር አቀፍ የስርአተ ጽህፈት ጉባኤ ተካሄደ !
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘገጀው አገር አቀፍ የስርዓተ ጽህፈት ጉባኤ ግንቦት 23/2010 ዓ.ም በጌት ፋም ሆቴል ሲያካሂድ በጉባኤው ላይ ከክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ በአገር ውስጥ ካሉ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የተወጣጡ የዘርፉ ምሁራን፣ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በጉባኤው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከስርዓተ ጽህፈት ማበልጸግና መጠቀም ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎች በዘርፉ ምሁራን ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል ፡፡ The Oromo alphabet in LAGIM በአቶ አበበ ቀኖ፣ The Ethiopian writing system and its contributions to Ethiopian nationhood በዶ/ር አየለ በክሪ፣ የኽምጣጋ ቋንቋ የስርዓተ ጽህፈት ቅኝት የፊደል ገበታ ዝግጅት በዶ/ር ሸጋው ወዳጅ እና በ ዶ/ር መለሰ ገላነህ፣ ለኦሮሚኛ ስርአተ ጽህፈት ላቲን ወይስ ፊደል በአቶ ዝናወርቅ አሰፋ ከቀርቡት ጥናታዊ ጽሁፎች መካከል ይገኙበታል፡፡
በመጨረሻም ተሳታዎች ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያት እንደዚህ አይነት በጥናት ላይ ተመስርተው የሚቀርቡ ጽሁፎች በቀጣይ በተለያዩ ሀገሪቷ ውስጥ ባሉ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ለሚደረጉ ጽሁፎችና የፊደል ገበታ ዝግጅቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አስተያየታቸውን እንደሚያደርጉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡
News and Updates
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!
- ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡
- ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡