የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በባህል ዘርፍ የመማክርት ጉባኤ /ቲንክ ታንክ/ ለመመስረት ከተለያዩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ሙሁራን ጋር ምክክር አደረገ፡፡

ግንቦት 16/2010 ዓ.ም. የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን የምክክር መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት እኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ የመነቃቃትና የጽናት መንፈስ ታጥቀን ሀገራችንን እንድንገነባ ታላቅ ደወል የተደወለበት ወቅት ነው፡፡ ይህን እውን ለማድረግ እያጣጠምን ያለነውን ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ለማስቻል የባህልና የኪነ-ጥበብ እንዲሁም የቱሪዝም ባለሞያዎች ሚና የጎላ በመሆኑ ይህንን የመማክርት ጉባኤ በማዘጋጀት አገራዊ አስተሳሰብን ተግባራዊ ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ሙሁራን በበኩላቸው ለእንደዚህ አይነት ሀገራዊ አጀንዳ ታስፈልጋላችሁ ተብለው መጋበዛቸው እንዳስደሰታቸው እና ሀሳቡ አሁን ላለንበት ወቅት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተደራጀ እና በተጠና መንገድ በፍጥነት ወደ ተግባር መገባት እንዳለበት ተናግረው አሁን ሀገራችን ያለችበት ጥሩ የለውጥ እና የመነሳሳት ስሜት የኪነ-ጥበብ ባለሙያውና ሙሁራኑ ለዘርፉ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ መንገድ የከፈተ በመሆኑ ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎታቸው እንደሆነ ተናግረዎል፡፡


የመማክርት ጉባኤ የባህል ፖለሲያችን አንድ አካል በመሆኑ ሚኒስቴር መስርያ ቤታችን ከባለሙያዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው፡፡ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያግዝ አንዱ መንገድ ይህ በመሆኑ በአፋጣኝ ወደ ተግባር ይገባል ብለዎል፡፡ በመጨረሻም የመማክርት ጉባኤውን ተግባራዊ ለማድረግ 10 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

 
 

News and Updates News and Updates