ሀገራችንን የሚጎበኙ ቱሪስቶችን ደህንነት ለመጠበቅ የቱሪስት ፖሊስ ማሰልጠን አዋጭ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡
ሀገራችንን የሚጎበኙ ቱሪስቶችን ደህንነት ለመጠበቅ የቱሪስት ፖሊስ ማሰልጠን አዋጭ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡
ህዳር 07/2010 ዓ.ም. የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የቱሪስት ደህንነትን በተመለከተ በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት አደረጉ፡፡
አውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት በኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ መዓዛ ገብረ መድህን ሲሆኑ በንግግራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እያደገ የመጣውን ሀገራችንን የሚጎበኙ ቱሪስቶችን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲህ አይነቱ ጥናት አስፈላጊና ወቅታዊ ነው ብለዉ ይህም ተግባራዊ እንዲሆን የክልልና የፌዴራል ፖሊስ ተቋማትና ባለ ድርሻ አካላት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ ለተግባራዊነቱ ሁሉም በንቃት መስራት አለበት ብለዋል፡፡
ጥናቱን ያዘጋጁት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባለሙያ ኢንስፔክተር ዳምጠው ዉዱ እንዳሉት በቱሪስት ደህንነት ዙሪያ የተሰራ ጥናት ይህ የመጀመርያው እንደሆነ ተናግረዉ በርካታ ሀገራት ጥናቱን አካሂደው በቱሪዝም ማርኬቲንግ ስራዎቻቸው ጭምር በማካተት ተጠቃሚ ሁነዋል፡፡ ሀገራችንም እያደገ የመጣውን የቱሪስት ቁጥር ደህንነት ለመጠበቅ ወቅቱ አሁን በመሆኑ ይህ ጥናት እንደተዘጋጀ ተናግረው ጥናቱም ከኬንያ፣ከአሜሪካ፣ከሞሮኮ እና ከማሌዥያ ልምድ የተወሰደ ነው ብለዋል፡፡
ሀገራችንን በሚጎበኙ ቱሪስቶች ላይ በተደረገ ጥናት እንደሚያመላክተው 57% ያለ ስጋት እንደሚቀሳቀሱ ተናግረው 43% ስጋት አለብን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በተያያዘም ቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ሲደርስባቸው ለፖሊስ ከማሳወቅ ይልቅ ለአስጎብኝዎችና በአከባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች የሚያመላክቱት ይበልጣል ይህም የሚያሣየው በዘርፉ ገና መሰራት ያለበት ስራ እንዳለ የሚያመላክት መሆኑን ገልፀዋ፡፡
በአውደ ጥናቱ የተሳተፉ ባለ ድርሻ አካላት እንደተናገሩት ጥናቱ ሀገራችንን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች ወቅታዊ ሁኔታ በሚገባ የዳሰሰ እንደሆነና ጥናቱ ከወረቀት ወርዶ ወደ ተግባር መግባት አለበት ብለው የቱሪስት ሴኪዩሪቲ ፖሊስ ማዘጋጀት አዋጭ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
News and Updates
- The Geda Panel discussion held on the 4th anniversary of the Geda system recorded in the world heritage
- በአንኮበር ወረዳ በጎረቤላ ከተማ ተገንብቶ ለተመረቀው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየም የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶች ተበረከቱለት
- ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!
- ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡
- ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡
- የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሣው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- ስፖርት ለሰላም! በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
- ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
- የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም ሙዚየም በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡