በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ታሪክ ላይ ትኩረት ያደረገ መፅሃፍ ተመረቀ

ጥቅምት 17 ቀን 2010 . በኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ታሪካዊ ዳራና ነባራዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ መፅሀፍ የዘርፉ ተዋንያን በተገኙበት በገነት ሆቴል አዳራሽ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመረቀ፡፡

የምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማስልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሸብር ተክሌ እንዳሉት የዚህ አይነት መፅሃፍት የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም በሚያደርገው ጥራቱን የጠበቀና የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት ሂደት ውስጥ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን በማመን እንደሚያበረታታ ገልፀዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳና መፅሃፉን በይፋ የመረቁት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም ሲሆኑ የመፅሃፉ ባለቤት አቶ ማቴዎስ ጡሜቦ በስራ ዘመናቸው ያካበቱትን ልምድና እውቀት በዚህ መልኩ ሰንደው ለዘርፉ በማበርከታቸው አመስግነው፤ በተለይም ባለፉት ዘመናት በዘርፉ ገንቢ አሻራዎችን ጥለው ያለፉ አካላትንና አጠቃላይ ለዘመኑ ትውልድ አስተማሪ ሆኖ የቀረበ መፅሃፍን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በተለይ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ላይ የተሰማሩ አካላት በዚህ ምልኩ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ሰነዶች ለማስተማሪያና ለጥናትና ምርምር መነሻ አድርገው መውሰድ የሚችሉት መፅሃፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የመፅሃፉ ደራሲና የሆቴል ባለሙያው አቶ ማቴዎስ ጡሜቦ 1898-2009 . የኢትዮጵያ የሆቴል ታሪክ ከሚዳስሰው መፅሃፋቸው ውስጥ ካሰፈሩት ቁም ነገር የተወሰኑትን ለታዳሚያን በማቅረብ የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተጠናቋል፡፡


News and Updates News and Updates