የመስቀል በዓል-የኢትዮጵያና የአለም ቅርስ በድምቀት ተከበረ

የመስቀል በዓል በአገራችን በኢትዮጵያ በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን ይከበራል፡፡ የበዓሉ አከባበር መነሻ ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በአይሁዶች ከተቀበረ በኋላ የሮማዊው ንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት በሆነችው በንግሥት እሌኒ መስቀሉ ከተቀበረበት ቦታ የእንዲወጣ ቁፋሮ የተጀመረበትን ቀን በማሰብ ነው፡፡

(በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮት መሠረት መስቀሉ ተቆፍሮ የወጣው መጋቢት 10 ቀን ሲሆን መስከረም 17 ቀን መስቀሉን ለማውጣት ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ነው)፡፡

በዓሉ በአገራችን ሁሉም አካባቢዎች በአብዛኛው ተመሳሳይ አይነት አከባበር ሲኖረው በየዓመቱ መስከረም 17 ሌሊት ላይ (በአንዳንድ አካባቢዎች ለበዓሉ የተዘጋጀውን ደመራ በመለኮስና በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል፡፡ የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ 1600 ዓመታት በላይ ሃይማታዊ ትውፊቱን እና ሥርዓቱን እንደጠበቀ የዘለቀ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ የባህል ተቋም (UNESCO) ... 2013 የመስቀል በዓልን የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ (Intangible Heritage) አድርጎ መዝግቦታል፡፡ ዘንድሮም በዓሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በድምቀት ተከብሯል፡፡

 

 


News and Updates News and Updates