በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች ደረጃ ምደባ ይፋ ሆነ።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ጋር በጋራ በኢትዮጵያ የሚገኙNewsየሆቴሎች ደረጃ ምደባ ሲያካሂድ መቆየቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ታደለች ዳላቾ ገለጹ፡፡ የደረጃ ምደባው በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልል የሚገኙ ሆቴሎችን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ታደለች ዳላቾ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም መ/ቤቱ አዳራሽ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሆቴሎች 136 ተለይተው 123 ሆቴሎችን መመዘን ሥራ ተሠርቷል፡፡ ነሀሴ 2 ቀን 2007 ዓ.ም የተመዘኑበትን ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ሆቴሎቹ ያላቸውን የምዘና ውጤት አይተው ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን በተዘጋጀው የቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት መሠረት ለአለም የቱሪዝም ድርጅት ቀርቦ መጀመሪያ የመደበው አካል ሳይሆን ሌላ አካል አይቶ ለቅሬታቸው ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ከተለዩት 123 ሆቴሎች 68ቱ የምዘና መሥፈርቱን አሟልተው በደረጃ ምደባው ተካተዋል፡፡

የደረጃ ምደባውን ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩት ጄምስ ማክ ግሪጎር እንደገለጹት የኮከብ ደረጃ ምደባው ከዓለም ቱሪዝም ድርጅት፣ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ከአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን፣ ከአዲስ አበባ ምግብ መድሀኒትና ጤና እክብካቤ አስተዳደር ኤጀንሲ ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን እየሠሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

አያይዘውም ለደረጃ ምደባው በዓለም ላይ ያለውን የሆቴል ደረጃ ምዘና አሰጣጥ ስታንዳርድ የተዘጋጀውን መሥፈርት የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ባለሙያው ገለጻ ከ12ቱ ዋና ዋና መስፈርቶች የሆቴሎች የንጽህና ጉዳይ ቀዳሚ ሲሆን የአደጋ ጊዜ መውጫና መሠብሰቢያ፣ የመጠቀሚያ ቁሳቁሶች አያያዝና ንጽህና፣ ምንጣፍና

አልባሳት፣የሠራተኞች ሁኔታና አያያዝ የመኝታ ቤት ንጽህና የመሣሠሉት ከመስፈርቶቹ መካከል የሚጠቀሱ ሲሆኑ በአብዛኖቹም እነዚህ በጉድለት ታይተዋል ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዘርፉ የሠለጠነ የሠው ኃይል ውስንነት እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

የምዘና ሰርዓቱ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ በተሠጠው ሥልጣን መሠረት ደረጃ ያገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሠጪ ተቋማት እንደገና ደረጃቸው በ3 ዓመት ውስጥ እንዲታይና የአገልግሎት አሠጣጣቸውን እንዲመዝን የሚፈቅድ በመሆኑ አሁን ምዘና ተደርጎላቸው የኮከብ ደረጃ የተሠጣቸው ሆቴሎች በየ3 ዓመቱ እንደገና ምዘና የሚደረግላቸው ሲሆን በዚህ መካከል በተሠጣቸው መስፈርት መሠረት ደረጃቸውን ለማሻሻል የሚፈልጉ ሆቴሎች ምደባ ከተሠጠ ከ1 ዓመት በኋላ ክለሳ እየተደረገ ደረጃቸውን ማሳደግ እደሚችሉም ይህ የአሰራር ሥርዓት እንዳለ ክብርት ወ/ሮ ታደለች ጠቁመዋል፡፡

ባጠቃላይ ከተመዘኑት 68 ሆቴሎች ውስጥ 4 ባለ አምስት ኮከብ፣ 13 ባለ አራት ኮከብ፣ 25 ባለ ሦሥት ኮከብ፣ 19 ባለ ሁለት ኮከብ እና 7 ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ እንደተሠጠ ተገልጻል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በኮከብ የተመደቡ ሆቴሎች ያገኙት ውጤት በዝርዝር

ተ.ቁ የሆቴሉ ስም ያገኙት ኮከብ ደረጃ
1. ሸራተን አዲስ ሆቴል 5 ኮከብ
2. ኢሊሌ ሆቴል 5 ኮከብ
3. ካፒታል ሆቴል 5 ኮከብ
4. ራዲሰን ብሉ ሆቴል 5 ኮከብ
5. ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል 4 ኮከብ
6. ሐርመኒ ሆቴል 4 ኮከብ
7. ድሪምላይነር ሆቴል 4 ኮከብ
8. ጁፒተር ሆቴል (ካሳንቺስ) 4 ኮከብ
9. ሳሮማሪያ ሆቴል 4 ኮከብ
10.   ደብረ ዳሞ ሆቴል 4 ኮከብ
11.   ናዝራ ሆቴል 4 ኮከብ
12.   ፍሬንድሺፕ ሆቴል 4 ኮከብ
13.   ኔክሰስ ሆቴል 4 ኮከብ
14.   ዋሽንግተን ሆቴል 4 ኮከብ
15.   ሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል 4 ኮከብ
16.   ጁፒተር ሆቴል (ቦሌ) 4 ኮከብ
17.   ተገን ገስት አኮሜዴሽን ሆቴል 4 ኮከብ
18.   ዘሪዚደንስ ሆቴል 3 ኮከብ
19.   ኡማ ሆቴል 3 ኮከብ
20.   ሒልተን አዲስ ሆቴል 3 ኮከብ
21.   ሲዮናት ሆቴል 3 ኮከብ
22.   ቢርጋርደን ኢን ሆቴል 3 ኮከብ
23.   አዲስ ሪጀንሲ ሆቴል 3 ኮከብ
24.   ኢምቢልታ ሆቴል 3 ኮከብ
25.   አፍሮዳይት ሆቴል 3 ኮከብ
26.   ኪንግስ ሆቴል 3 ኮከብ
27.   ዋሳማር ሆቴል 3 ኮከብ
28.   ካራቫን ሆቴል 3 ኮከብ
29.   በሻሌ ሆቴል 3 ኮከብ
30.   ሞናርክ ሆቴል 3 ኮከብ
31.   አዲሲኒያ ሆቴል 3 ኮከብ
32.   ቶፕ ቴን ሆቴል 3 ኮከብ
33.   ክራውን ሆቴል 3 ኮከብ
34.   አምባሳደር ሆቴል 3 ኮከብ
35.   ሲያን ሲቲ ሆቴል 3 ኮከብ
36.   ሲድራ ሆቴል 3 ኮከብ
37.   አራራት ሆቴል 3 ኮከብ
38.   ግሎባል ሆቴል 3 ኮከብ
39.   አዲስ ቪው ሆቴል 3 ኮከብ
40.   ካሌቭ ሆቴል 3 ኮከብ
41.   ፓኖራማ ሆቴል 3 ኮከብ
42.   ሶሎቴ ሆቴል 3 ኮከብ
43.   ትሪኒቲ ሆቴል 2 ኮከብ
44.   ሆሜጅ ሆቴል 2 ኮከብ
45.   ደሳለኝ ሆቴል 2 ኮከብ
46.   ራስ አምባ ሆቴል 2 ኮከብ
47.   ፓስፊክ ሆቴል 2 ኮከብ
48.   ኢምፓየር አዲስ ሆቴል 2 ኮከብ
49.   ቸርችል ሆቴል 2 ኮከብ
50.   ግራንድ ዩርዳኖስ ሆቴል 2 ኮከብ
51.   ኬዜድ ሆቴል 2 ኮከብ
52.   አክሱም ሆቴል 2 ኮከብ
53.   ግዮን ሆቴል 2 ኮከብ
54.   ንግስተ ሳባ ሆቴል 2 ኮከብ
55.   ቀነኒሳ ሆቴል 2 ኮከብ
56.   ዳሙ ሆቴል 2 ኮከብ
57.   ሶራምባ ሆቴል 2 ኮከብ
58.   አስትራ ሆቴል 2 ኮከብ
59.   ሀይሚ አፓርትመንት ሆቴል 2 ኮከብ
60.   ኤድና አዲስ ሆቴል 2 ኮከብ
61.   ዴስትኒ አዲስ ሆቴል 2 ኮከብ
62.   ኤጂ ፓላስ ሆቴል 1 ኮከብ
63.   ሰሜን ሆቴል 1 ኮከብ
64.   ኢትዮጵያ ሆቴል 1 ኮከብ
65.   ናርዳን ሆቴል 1 ኮከብ
66.   ኤም ኤን ኢንተርናሽናል ሆቴል 1 ኮከብ

News and Updates News and Updates