የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደገረ።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በየሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና በ2008 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸ ምግምገማ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ ጥቅምት 23 ቀን 2008 ዓ.ም የግማሽ ቀን ውይይት አደረገ፡፡

News

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትሮች  ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት


ውይይቱን የከፈቱት ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ሲሆኑ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከሴክተሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ወደ ውጤት እንደርሳለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዕለት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተገናኙበትን ዋና ዓላማ ሲገልጹ የሴክተራችንን የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የጋራ ለማድረግና ከእናንተ ጠቃሚ ግብዓቶችን ለማግኘት ነው ብለዋል፡፡ በዋና ዋና ዕቅዱ ላይ ውይይት በማድረግ አስፈላጊውን ግብዓት በመውሰድ ዕቅዱን ለማዳበር ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡ በመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከሚኒስቴር መ/ቤታችን ጋር በጋራ አቅዳችሁ በጋራ ትሠሩ የነበረውን አሁንም አጠናክረን በመቀጠል በስራ ላይ የሚያጋጥሙን ተግዳሮቶች ቢኖሩ እንኳ የመንግስትን ህግና ደንብ ተከትለን ለመፍታት እንንቀሳቀሳለን ሲሉ በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡

News

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት እንደገለጹት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ታቅደው ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት የቀረበውን እቅድ አድንቀው ሁሉም ይህን እንደተልዕኮ ይዘው ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም በመድረኩ የተነሱ የተወያየንባቸው ነጥቦች እንዲሁ በውይይት የሚቀሩ እንዳልሆኑ እና በጋራ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በመሆን ያሉትን የመረጃ አያያዝና ሌሎችንም በዝርዝር ያላየናቸው አንኳር ጉዳዮች ላይ የጋራ ትስስር በመፍጠር፣ አቅዶ በጋራ ለመስራት፣ ሀብትን በጋራ ለመጠቀም፣ የባለሙያና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ፣ ሪፖርት ዕቅድንና አፈጻጸምን በቋሚ የግንኙነት ጊዜያት በጋራ ለመገምገም የሚያስችል አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


News and Updates News and Updates