ዜናን ምምሕያሻትን

ስፖርት ለሰላም! በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

ታህሳስ 03/2011 ዓ.ም በኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴርና የሰላም ሚንስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው የምክክር ስነ-ስርዐት ላይ ከሁሉም ክልሎች፣ ከስፖርት ፌደሬሽኖች፣ ማህበራት፣ ባለሙያዎች፣ ደጋፊዎችና ስፖርተኞች ተሳትፈዋል። በመድረኩ ላይ በዋናነት በተለያዩ ቦታዎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች፣ የቡድን መሪዎችና አመራሮች ህግና መመሪያዎችን በአግባቡ ባለመተግበር በሚፈጥሯቸው ችግሮች የስፖርት ማህበረሰቡ እየተረበሸ መሆኑ ተነስቷል።

ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ታህሳስ 02/2011 ዓ.ም በኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን ጋር በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትሯ እንዳሉት ሀገራችን ያላት እምቅ የተፈጥሮ፣ የባህልና የታሪክ ሀብት መልማትና መጠበቅ የሚገባው ሲሆን በተለይ ኳታር በባህል ማዕከል/መንደር፣ የስፖርት ተቋማት ግንባታ፣ በእስልምና ሙዚዬም አደረጃጀት ላይ ያላት ልምድና ተሞክሮ ወደ ሀገራችን ሊሰፋ የሚገባው በመሆኑ በቀጣይ አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም ሙዚየም በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡

በዳግማዊ አፃ ምኒሊክ የተመሰረተችውና 126 ዓመታትን ያስቆጠረችው የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም በአዲስ መልክ ያደራጀችውን ሙዝየም ለጎብኚዎቸ ክፍት በተደረገበት ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ይህንን ጥንታዊና ታሪካዊ ንዋየ ቅዱሳንን የያዘ ገዳም ጠብቀውና ተንከባክበው ለዚህ ትውልድ ያስተላለፉትን የገዳሙ አባቶችና የአዲስዓለም ከተማ ነዋሪዎች ሊመሰግኑ ይገባል ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ መስከረም 28/2011 በኢትዮጵያ ጥንታዊ የፅሁፍ ኃብት ያለበትን ሁኔታ የመፈተሽና ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት የመቀየስ ዓላማ ያለው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ጉባዔ በአዲስ አበባ ተከፈተ።

የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲ ወደ ተግባራዊ እቅስቀሴ ተሸጋገረ፡፡

መስከረም 29 ቀን 2011ዓ.ም የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲን ለመተግበር እና የማስፈጸሚያ ስልት ለመንደፍ የተዘጋጀ መድረክ በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ሠላም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ፊልም ፕሮዲውሰሮች ማህበር ትብብር አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ - መዛግብትና ቤተ - መጻሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ተካሄደ፡፡