የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ያዘጋጀውን “የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መቆጣጠሪያ ሥርዓት” በይፋ ስራ አስጀመረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ መቆጣጠሪያ በይነ መረብ ያዘጋጀውንየኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መቆጣጠሪያ ሥርዓትከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በይፋ ስራ አስጀምሯል፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በይነ መረቡን በተረከቡበት ጊዜ ባደረጉት ንግግር እንደዚህ አይነት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሽታውን ለመከላከል ለሚደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
በይነ መረቡ በሀገር አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ ከኮሮና ጋር ተያያዥ የሆኑ የእየለቱን ጉዳዮች መረጃ ለመሰብሰብ ያስችላል፡፡
ከሆስፒታሎች፣ ከህክምና ቁሳቁሶችና ከኮሮና ጋር የተገናኙ ሌሎች መረጃዎች በበይነ መረቡ ላይ ሰፍሯል፡፡
በይነ መረቡ ሀገር ውስጥ የገቡ መንገደኞችን በጂፒኤስ መቆጣጠር ያስችላል ተብሏል፡፡
ኢንተርኔት በሌለበት ቦታ በስልክ እንደሚሰራ እና በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ሲሆን ወደፊት በሌሎች ቋንቋዎች እንደሚዘጋጅ ታውቋል፡፡


News and Updates News and Updates