የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል 84.5% ሰራተኞቹ ላልተወሰነ ጊዜ በቤታቸው ሁነው እንዲሰሩ ወሰነ፡፡

መጋቢት 15/2012 .
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ከነገ መጋቢት 16/2012 . ጀምሮ ስራቸውን በቤታቸው በመሆን እንዲያከናውኑ ባወጣው አስቸኳይ መመሪያ መሰረት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርም መመሪያውን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፣በዋናው መስሪያ ቤት ከሚሰሩ አጠቃላይ 377 ሰራተኞች መካከል በስራቸው ባህርይ ምክንያት 86 ሰራተኞች ብቻ በስራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ውሳኔው ለሚ/ /ቤቱ ተጠሪ በሆኑ ተቋማት ላይም ተግባራዊ ሲደረግ 307 አጠቃላይ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን /ቤት ከሚሰሩ ሰራተኞች መካከል 19 ሰራተኞች ብቻ፣ከ307 የብሄራዊ ቲአትር ሰራተኞች መካከል 14 ሰራተኞች 215 የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም ሰራተኞች መካከል 28 ሰራተኞች፣ 310 የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል 57 ሰራተኞች እንዲሁም 218 የስፖርት ኮሚሽን ሰራተኞች መካከል 42 ሰራተኞች ብቻ በስራ ገበታቸው እንዲገኙ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

በአጠቃላይ በዋናው መስሪያ ቤትና በተጠሪ ተቋማት ከሚገኙ 1655 ሰራተኞች ውስጥ 1399(84.5 %)
የሚሆኑ ሰራተኞች ስራቸውን በቤት ውስጥ በመሆን እንዲያከናውኑ ሲደረግ 246 ሰራተኞች ግን መደበኛ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ተደርጓል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በየጊዜው የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመቆጣጠር ሁላችንም ሃላፊነታችን እንወጣ!!!


News and Updates News and Updates