የጥበብ ሙያተኞችና የመገናኛ ብዙሃን ኮቪድ 19 ቫይረስ በሀገራችን የሚኖረውን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራን ነው አሉ፡፡

የተለያዩ የኪነ-ጥበብና እና ስነ- ጥበብ ማህበራት መሪዎች፤ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አመራሮችና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም የጠቅላይ ሚንስቴር ቢሮ እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካዮች በጋራ ባደረጉት ውይይት በዚህ ወቅት ማህበረሰቡን የሚያስተምሩና የሚያዘጋጁ ስራዎች አስፈላጊ እንደመሆናቸው ተቀናጅቶ መስራት እንደሚጠይቅ ተገልጧል፡፡
በተለይም የሚተላለፉ መልዕክቶች አዝናኝነት ሲኖራቸው የበለጠ ውጤታማ ስለሚሆኑ የጥበብ ሙያተኞች በዚህ ረገድ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጧል፡፡


በሽታው አዲስ እንደመሆኑ ህበረተሰቡ እንዳይዘናጋ ግን ደግሞ በተጋነነ መልኩ በማየት አላስፈላጊ መረበሽ ውስጥ ሳይገባ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማስቻል ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡ ይህንን በፊልም፣ በሙዚቃ፣ በስዕል፣ በኮሜዲ፣ በቴአትርና መሰል ጥበባት ማገዝ ተገቢ ነው ያሉት ተወያዮቹ በጅምር ላይ ያሉ በርካታ ስራዎች መኖራቸውንም አንስተዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት / ሂሩት ካሳው ሚዲያዎችና እና የኪነ ጥበብ ሰዎች በርካታ ተከታዮች ስላሏቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላሉ ብለዋል፡፡


የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሪታሪ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው ሁሉም እንደየችሎታው ማገልገል እንዳለበት አሳስበው በመንግስት በኩል እየተወሰዱ ያሉ በርካታ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ ችግሩ እየተባባሰ የሚሄድ ከሆነ በሚልም መንግስት ሰፋፊ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በበተለይ ወቅቱ በትብብር እና በመተጋገዝ መስራትን ስለሚጠይቅ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት / ብዙነሽ መሰረት የሚመራ ቡድን ተቋቁሞ ክትትል እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡


News and Updates News and Updates