ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ#ኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

መንግሥት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ጊዜ የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋጽኦ የሚፈልግ ነው። እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ስናልፍ፣ በድል አድራጊነት ለመወጣት የሚያስችሉን በኅብረት እና በሚገባ በመቀናጀት የምናደርጋቸው ጥረቶች ብቻ ናቸው። ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ' በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው #ኮቪድ19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ለግሰዋል።

'ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ' በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ ብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው #ኮቪድ19 አቅርቦት ማሰባሰቢያ ለግሰዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed launched a national resource mobilisation committee tasked with coordinating efforts of gathering financial and non-financial materials for #COVID-19 emergency preparedness. While the government has allocated a significant budget and is mobilising resources to prepare for the worst case scenario, such periods require the effort and contribution of each individual. Our collective and concerted efforts to help one another in times of great need will be the only way we overcome.

Modeling the effort to ‘keep calm and contribute’ the national committee members have donated their one month salary to the National #COVID-19 resource pool.

#PMOEthiopia


News and Updates News and Updates