መልዕክተ ትንሳኤ!!

ክቡራንና ክቡራት...
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለምትገኙ መላ ኢትዮያውያን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ-ትንሳኤው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ በዓሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የሚታሰብበት እንደመሆኑ ሁላችንም የልቦና ትንሳኤ እንዲኖረንና ሥርዓተ ዕምነቱ በሚፈቅደውና በሚያዝዘው፤ እንዲሁም የቀደምት አበውን ባህላዊ ትውፊት ተቀብለን ምዕመናን እንደየአቅማችን የታመሙትን ወገኖች በመጠየቅ፣ ለተራቡት በማካፈል፣ ለታረዙት በማልበስ፣ የታሰሩትን በመጠየቅና በመሳሰሉት የበጎ ምግባር መገለጫዎች ተሸልመን በደስታ ማሳለፍ ይኖርብናል፡፡ ይልቁንም ያለንበት ወቅት ዓለማችንም ሆነ አገራችን በCOVID-19 ወረርሽኝ የተነሳ በታላቅ ፈተና ላይ የምንገኝ እንደመሆኑ ችግሩን ለመከላከል እንዲቻል ለሃይማኖት አባቶችም ሆነ ለመንግስት ምክርና ትዕዛዝ ተገዥዎች በመሆን ይህንን ክፉ ጊዜ በጥበብና በብልሃት እንዲሁም በፍቅርና በመረዳዳት ለማለፍ የየበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ አደራ ለማለት እንወዳለን፡፡ ይህንን ማድረግ ከቻልን አፅዋማቱንና ስግደቱን አልፈን የጌታን ትንሳኤ እንደምናከብር ሁሉ ችግሩን በሁላችንም ትጋትና በእግዚአብሔር ቸርነት ተሻግረን የአገራችንን ትንሳኤና ብልፅግና ዕውን እንደምናደርግ ጥርጥር የለንም፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከዚህ ፈታኝ ጊዜ አሻገሮ በአንድነትና በፍቅር አገራችንን ለመገንባት ዳግም የምንተጋበትን ጊዜ ያሳዬን፡፡
ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

News and Updates News and Updates