የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተከበረ

ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በሀገራችን ለ13ኛ ጊዜ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ‹‹ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለአገራዊ ብልፅግናችን!›› በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም ተከብሯል፡፡
ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ታሪካችን እና የአብሮነታችን ማሳያ በመሆኑ እና ለቀጣይም የሰላማችንና የብልፅግናችን ማረጋገጫ ሁኖ እንዲቀጥል በየዓመቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው የአከባበር መመሪያ መሰረት ከፌደራል እስከ ክልል ባሉ ተቋማት በድምቀት ይከበራል፡፡
የዘንድሮው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀንም ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰንደቅ ዓላማችን በብሔራዊ መዝሙራችን ታጅቦ እንዲሰቀል በታዘዘው መሰረት የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች ክቡር አቶ ሐብታሙ ሲሳይ የኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
‹‹ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለአገራዊ ብልፅግናችን!››