የባህልና ቱሪዝም ዘርፍን እንዲመሩ የተሾሙ ሚኒስትሮች ከመ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ
ግንቦት 8/2010 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ - መዛግብትና ቤተ - መጻህፍት ኤጀንሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የትውውቅ መድረክ ላይ ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር፣ የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እና ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አጠቃላይ መካከለኛ አመራሮች እና ፈጻሚዎች ጋር ትውዉቅ አድርገዋል፡፡
ዘርፉን በመምራት ሂደት በሚኖራቸው ቆይታ በሴክተሩ በየደረጃው ያሉ ችግሮችን በመለየት ክፍተቶችን በማስተካከል እና የነበሩትን መልካም ጅምሮች አጠናክሮ በማስቀጠል ላይ እንደሚያተኩሩ ጠቁመው ለዚህም ሁሉም የሚ/ር መ/ቤቱ ሰራተኞች ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በቀጣይ በሚ/ር መ/ቤቱ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር ለማስፈን ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የሚ/ር መ/ቤቱ ሠራተኞች የለውጥ መሳሪያዎችን በሚገባ ተረድተው ተግራዊ በማድረግ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና በአዲስ የሥራ መንፈስ ወደ ተግባር በመግባት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ መትጋት እደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
News and Updates
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡
— 10 Items per Page
Chat
Chat is temporarily unavailable.