፲፪ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሰመራ ከተማ ተከበረ፡፡

           ፲፪ኛው  የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሰመራ ከተማ  ተከበረ፡፡

የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት የፀደቀበትን ፳፫ዓመት እና የብሔር ብሔረ-ሰቦች ቀን ፲፪ ዓመት በዓል አከባበር በህገ-መንግሥታችን የደመቀ ህብረ-ብሔራዊነታችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል ከህዳር ፳፮ እስከ ፳፱/ ፪፼፲ በልማታዊ ኤግዚቢሽን፣ በንግድና ባዛር በሲምፖዚየም፣ እንዲሁም በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ በክልሉ መዲና ሰመራ ከተማ ተከብሯል፡፡

ለዚህ ታላቅ በዓል ሰፊ ዝግጅት በማድረግ እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ህዝቡ ለመላው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ህዝቦች ያለውን ክብርና ፍቅር ወገናዊነቱን በግልፅ ያሳየበት ነበር፡፡

የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች በህገ-መንግስቱ አማካኝነት የተጎናጸፏቸውን ድሎች እውን ከሚያደርጉባቸው አደረጃጀቶች መካከል ከግንባር ቀደሞቹ ተርታ ተጠቃሽ በመሆኑ በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚከናወኑ የማስተዋወቂያ ሥራዎች ላይ የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን መልካም ገጽታ በመገንባት ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን ሁኔታዎች መፍጠር ላይ በማተኮር የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በዚህም ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች በተከበሩ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ተሳትፎ በማድረግ ተልዕኮውን ለመወጣት የተንቀሳቀሰ ሲሆን  ዘንድሮም በአፋር ብሔራዊ ክልል በሰመራ ከተማ በድምቀት በተከበረው በዓል አካል በነበረው የልማት ኤግዚቢሽን ላይ የሚኒስቴር መ/ቤት ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴን በማካተት  አጠቃላይ የዘርፉን እንቅስቃሴ ሊያሳይ በሚችል መልኩ   ከፍተኛ የሆነ የማስተዋወቅ ስራ አከናውኗል፡፡

 


News and Updates News and Updates