በታላቁ የግሪክ ፈላስፋ የህይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ “ባዶ እግር” የተሰኘ ቴአትር ተመረቀ

 

ጥቅምት 21 ቀን 2010 .ም. በአሜሪካዊው ፀሀፊ-ተውኔት መምህርና ጋዜጠኛ ማክስቴል አንደርሰን .. 1952 የተፃፈውና በአስቻለው ፈቀደ ተተርጉሞ ለእይታ የበቃው ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ በሶቅራጥስ የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ያተኮረ ባዶ እግር ”Barefoot in Athens“ የተሰኘው ቴአትር በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር አዳራሽ የግሪክ ሪፐብሊክ ማህበረሰብ፣ የተለያዩ የዲፕሎማቲክ አካላት፣ እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የጥበብ አፍቃርያን በተገኙበት ተመረቀ፡፡

የኢትዮጵያና የግሪክ ሁለትዮሽ ግንኙነት መቶኛ ዓመት በማስመልከት በተመረቀው ቴአትር በሁለቱ አገራት ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የግሪክ መንግስትን በመወከል በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር ኒኮላስ እንደገለፁት ... 1917 የጀመረው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የጋራ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እተሸሻለ መጥቷል፡፡ በተለይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሯል፡፡ ይህን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማስቀጠል የጥበብ ስራዎች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑንና በቀጣይም በጋራ እንደሚሰሩ በመግለፅ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ምስጋናቸውን እና ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ መንግስትን በመወከል ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም በንግግራቸው 100 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮጵያና ግሪክ ግንኙነት በርካታ ቁጥር ያላቸው ግሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮጵያዊ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር አብረው በመኖር በተለያዩ የንግድና የባህል እንቅስቃሴዎች በመሳተፋቸው በሁለቱም አገራት መካከል ያለንን የጋራ ባህል ውርስን ልንጋራ ችለናል፡፡

 

አያይዘውም ቀድሞ የነበረውን የቆየ ታሪካዊ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ጊዜው አሁን በመሆኑ እንደዚህ አይነት የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ማከናወን በተለይ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር አቅም የሚፈጥርና ለወደፊቱ ትውልድ የሚያነሳሳ ኃይል ነው፡፡ የጥንት ፈላስፋዎች የህይወት ልምድ በዚህ መልኩ ለእይታ መብቃቱ ተምሳሌያዊነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ በማለት አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኘው የግሪክ ሪፑብሊክ አባላት መልካም ምኞታቸውን በመግለፅባዶ እግርየተሰኘው ቴአትር መመረቁን ይፋ አድርገዋል፡፡

 

2 ሰዓት 20 ደቂቃ ያህል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ለእይታ የበቃው ባዶ እግር ቴአትርን አስቻለው ፈቀደ በተርጓሚነት፣ ራሔል ተሾመ መሐመድ በዋና አዘጋጅነት፣ ታላቁ የጥበብ ሰው አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ የድርሰት አርትኦት ሚናቸውን ሲወጡ በነሱ ስራ ላይ ነፍስ የዘሩት ተዋንያን ደግሞ ኤልሳቤጥ መላኩ፣ስዩም ተፈራ፣ ተስፋዬ /ማርያም ጌታቸው ስለሺ፣ ሰለሞን ተካ፣ ዋሲሁን በላይ፣ ማህተመ ኃይሌ፣ ሄኖክ ዘርዓብሩክ፣ አልጋነሽ ታሪኩ፣ ንጉሴ በላይ፣ ዳንኤል ብርሐኑ፣ ጌትነት ተካ፣ የማታወርቅ ታደሰ፣ መርዕድ ተስፋዬ፣ ታሪክ አስተርዓየ፣ ቅድስት ብሩክ ክሽን አድርገው ተውነውታል፡፡ በቀጣይ ዘወትር እሁድ 800 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለእይታ እንደሚበቃ ለማወቅ ተችሏል፡፡


News and Updates News and Updates