የመስቀል በዓል-የኢትዮጵያና የአለም ቅርስ በድምቀት ተከበረ
የመስቀል በዓል በአገራችን በኢትዮጵያ በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን ይከበራል፡፡ የበዓሉ አከባበር መነሻ ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በአይሁዶች ከተቀበረ በኋላ የሮማዊው ንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት በሆነችው በንግሥት እሌኒ መስቀሉ ከተቀበረበት ቦታ የእንዲወጣ ቁፋሮ የተጀመረበትን ቀን በማሰብ ነው፡፡
(በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮት መሠረት መስቀሉ ተቆፍሮ የወጣው መጋቢት 10 ቀን ሲሆን መስከረም 17 ቀን መስቀሉን ለማውጣት ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ነው)፡፡
በዓሉ በአገራችን ሁሉም አካባቢዎች በአብዛኛው ተመሳሳይ አይነት አከባበር ሲኖረው በየዓመቱ መስከረም 17 ሌሊት ላይ (በአንዳንድ አካባቢዎች ለበዓሉ የተዘጋጀውን ደመራ በመለኮስና በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል፡፡ የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ከ1600 ዓመታት በላይ ሃይማታዊ ትውፊቱን እና ሥርዓቱን እንደጠበቀ የዘለቀ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ የባህል ተቋም (UNESCO) እ.ኤ.አ. በ2013 የመስቀል በዓልን የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ (Intangible Heritage) አድርጎ መዝግቦታል፡፡ ዘንድሮም በዓሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በድምቀት ተከብሯል፡፡
News and Updates
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡
— 10 Items per Page