Oduu fi Foyya'iinsa

ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!

ታህሳስ 16/2011 ዓ.ም እንደ አክሱም፣ ላልይበላና ጎንደር ስልጣኔ ሁሉ የቀደምት አያቶቻችንን የኪነ- ህንጻ ጥበብ ሊያስዋጀን የሚችል እና የአሁኑ ትውልድ የኪነ-ህንፃ ጥበብ ማሳያ በመሆን ለሀገራችን የተበረከተ ኢትዮጵያዊ ማንነትን መሰረት አድርጎ በመሶብ ቅርፅ የተዘጋጀ አዲስ ህንፃ መዲናችን አዲስ አበባ ከ5-6 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ልታገኝ ነው፡

ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

ታህሳስ 16/2011 ዓ.ም ውይይቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተቋሙ ጋር ተደጋግፎ ለመስራት ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ መረዳት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ ክብርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሣው ዓላማውን በአጭሩ በመግለጽ ሰፊውን ሰዓት ለሰራተኞች እድል በመስጠት ማዳመጥ ላይ የተመሰረተ መድረክ ነበር፡፡

የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡

ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ እርስቱ ይርዳው ቀደም ሲል በሩሲያ ሀገር በተካሄደው 19ኛው የዓለም የወጣቶች እና ተማሪዎች ፌስቲቫል ውድድር ላይ የልዑካን ቡድን መርተው በመሄዳቸውና በተለያዩ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ተሳትፎ በሀገሪቱ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የተፈረመ ዲፕሎማና ሜዳሊያ አበረከተች፡፡ የእውቅና አሰጣጡ ስነ-ስርዓት ዛሬ በብሄራዊ ቤተ-መጽሐፍትና ቤተ-መዛግብት አዳራሽ ሲካሄድ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ሴቮሎድ ትካቼንኮ ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡

ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ሚስተር ሴቮሎድ ትካቼንኮ ከኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱ አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከተመሰረተ 120 ዓመታትን የተሻገረ መሆኑን በመግለፅ ይህን መልካም ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በባህል፣ በቱሪዝም እና በስፖርት ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተው ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሣው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

ታህሳስ 09/2011 ዓ.ም ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በመገኘት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ጽ/ቤት በነበራቸው ቆይታ በባህል፣ በቱሪዝምና ስፖርት ዘርፎች ላይ በጋራ በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን አዲስ አበባ ያላት እምቅ የባህል፣ የቱሪዝምና የቅርሶች አቅም ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም የሚበቃ መሆኑን ገልጸው የከተማዋ ዋነኛ ገቢና የስራ እድል መፍጠሪያ ሆኖ የሚያገለግለው የቱሪዝም ዘርፍ በመሆኑ የተለያዩ ተግባራትን በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል በማለት ገልጸዋል፡፡