News and Updates

የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ

የገዳ ስርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተከፈተበት ወቅት የዕለቱ እንግዳ የሆኑት የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ አገር ናት። ኦሮሞ ደግሞ አንዱ ነው ፣

የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ

ፓርኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርቀው ከፍተውታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በፓርኩ በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡

የቱሪዝም መለያ የሆነውን ምድረ ቀደምት (Land of origins) የማስተዋወቅ ስራ ዛሬም በጥንታዊቷ የአክሱም ከተማ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካህሳይና የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ብርክቲ ገ/መድህን በተገኙበት ቀጥሎ ውሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ

በሀገራችን በተበታተነ መልኩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሰርከስ ቡድን አባላት መስከረም 19/2013 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ባካሄዱት የምስረታ ጠቅላላ ጉባዔ "የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት" በሚል ስያሜ የአንድነት ማህበር መሠረቱ፡፡

የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።

በወርሀ ጥቅምት ጎብኝዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ የምትገኘው ሀገራችን ጎብኝዎች ወደ ሀገራችን በሚመጡበት ወቅት ባለሙያቹ ማድረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች በተመለከተ በሀገራችን ለሚገኙ ሼፎች በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ስልጠና ተካሂዷል ።