የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
የቴአትር ቤቱ አጭር ታሪካዊ ዳራ
የቴአትር ቤቱ አመሰራረት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በቀድሞ ስሙ” የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” ቴያትር ተብሎ የተመሰረተው በ1948 ዓ/ም ለንጉሱ 25ኛ ዓመት የንግሥ በዓል ማድመቂያነት ነው የሚለው ታሪክ ሁሉም የሚያውቀውነና የተለመደ አባባል ቢሆንም አንዳንድ ሰነዶች እነደሚያሳዩት ግን የቴአትር ቤቱ አመስራረት ታሪክ ከዚህ የላቀ ተልዕኮ እንዳለው ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
ጥንታዊ ጽሁፎችና የታሪክ ሰነዶች እነደሚገጹት በ1940ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት አከባቢ እነደፊልም ፣ መጽሔት፣ የሸክላ ሙዚቃና ቴኘ በመሳሰሉ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የምዕራባዊን እና የአሜሪካዊያን የባህል ተፅእኖ እያደገ የመጣበት ጊዜ ስሆን ፣የሀገራቸው ባህል እንዳይጠፋ ይሳሱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በአንድ በኩል ይህንን የባህል ወረራ ለማቋቋም በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ከአለም ኪነጥበብ እድገት ለመቀነስ እንዲቻል የሀገራችንን የኪነጥበብ ዘርፎች ማሳደግና ዘመናዊ ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አምነውበት ነበር ፡፡ ከዚሁም ጋር ፅዴያ የ በአንድ በኩል ይህንን የባህል ወረራ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ብሔራዊ የሀገር ፍቅርና የጀግንነት ስሜትን ለማጠናከር ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ የሀገር ፍቅርና የጀግንነት ስሜትን ለማጠናከር ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸውን ቁም ነገሮች እያዝናኑ በህዝብ ዘንድ ለማስረጽ ሙዚቃና ቴያትር ያላቸው ጉልበት በእጅጉ ስላመነበት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጥንስስ የሆነውን ሙዚቃና ቴያትር ቡድን ከ1943 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሥር አደራጅቶ እናደነበር የተገኙት ሰነዶች ይናገሩሉ፡፡
ይህ የሙዚቃና የቴያትር ቡድን የሚያቀርባቸው ዝግጅቶች በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን በማትረፋቸውና የተመልካችም ብዛት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩና የሀገሪቱ እድገትና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍ እያለ በመሄዱ አንድ ዘመናዊ ቴአትር ቤት በከተማው ውስጥ እንደሚስፈልግ ታመነበት፡፡ በመሆኑም በማስፈለጉ በክብር ብላታ ዘውጣ በላይነህ በዚያን ጌዜ የአዲስ አበባ ከንቲባ አማካይነት ጉዳዩ እንደገና ለግርማዊ ንጉሰ ነገሥት ቀርቦ የማዘጋጃ ቤት ተበዳሪ ፣ የገንዘብ ሚኒስተር አበዳሪ ሆነው ፋሽስት ኢጣሊያ /ከ1928-1933 ዓ.ም./ ሀገራችንን በወረረበት ዘመን በመዲናችን እንብርት ላይ ቺኒማ ማርኮኒ በሚል ስያሜ ከሲኒማ አዳራሽነት ጀምሮት የነበረውን ህንፃ ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ እንዲሰራ ተወሰነ ፤ የቴያትር ቤቱ ህንፃ ግንባታ ሥራ ለንጉሠ ነገሥቱ 25ኛ ዓመት የዘውድ ኢዩቤልዩ በዓል እንዲደርስ ትእዛዝ በመሰጠቱም በቀሪው አራት ወር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ለማጠናቀቅ ርብርቦሽ ተደርጎበት በ3.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡
የዛሪው የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቴያትር /የወቅቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴያትር /ህዳር 3 ቀን 1948 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን ከፈረንሳይ ሀገር የመጡ የባለቤት አርትስቶች ትርኢትና ለማዘጋጃ ቤቲ ወደ አዲሱ ቴአትር ቤት በተዘዋወሩ አርቴስቶና ሙዚቀኞች በተሰራ ዳዊትና ኦርዮን በተሰኘው ተውኔት የመጀመርያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የትርዒት ምዕራፍ ተከፈተ፡፡ በዕለቱ 1264 ተመልካቾች የመክፈቻ ትርኢቱን የተመለከተ ሲሆን ዕለቱም ለሃገራችን የቴያትር ታሪክ ልቦና ይነታዊ እምርቱ የታየበት ክስተት ሆነ፡፡