የሚኒስቴሩ መገለጫ የሚኒስቴሩ መገለጫ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ታሪካዊ ዳራ

ባህል

ከ1900ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት አንስቶ በኢትዮጵያ የማዕከላዊ መንግስት በተጠናከረና በተንሰራፋበት' የአውሮፓ ዘመናዊ ሥልጣኔ በሀገራችን ቀስ በቀስ ሥር መስደድና ተግባራዊ እየሆነ በመጣበት' ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ በፊትና በኋላ በተለይም ከነፃነት ድል በኋላ ዘመናዊ የባህል አመራር በተለያዩ የሚኒስቴርና የድርጅት መሥሪያ ቤቶች ሥር በተዘዋዋሪ አመራር ማግኘት ጀመረ፡፡

ዘርፈ-ብዙው የባህል እንቅስቃሴ ከነባሩ ትውፊታዊና ልማዳዊ የባህል አመራር ተላቆ ዘመናዊው የባህል አመራር ሂደት አስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ፍፃሜ ድረስ በተናጠልና በተበታተነ ሁኔታ ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ መሠረት የሆነውና የኢትዮጲያ ጥናታዊ ቅርሶች አስተዳደርን አካቶ በመያዝ “የህዝብ ቤተመጻህፍ ወመዘክር”በሚል ስያሜ በ1936 ዓ.ም የተቋቋመው የዛሬው የብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ፋና ወጊ ሲሆን በመቀጠልም "የትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር" ከመደበኛ የትምህርት ፕሮግራሙ ጎን'የአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/ቤትን ' የእቴጌ እጅ ሥራ / እደ ጥበብ / ት/ቤትን ' የተግባረ እድ ት/ቤትን'የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤትን ' የአማርኛ መርሐ ልሣንን በመመስረትና በመምራት እንዲቋቋም ተድርጎ እንደነበር ከሰነዶች መገንዘብ ይቻላል፡፡

"የማስታወቂያ“ መርሀ ብሄር ሚኒስቴር" ከመደበኛ የማስታወቂያ ሥራ ጋር' የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ማህበርን / ሀገር ፍቅር ቴአትር / ' የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር / የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር / እና የተለያዩ ሲኒማ ቤቶችን በመመሥረትና በመምራት ተቋቋመ፡፡

ይሁን እንጂ ለዘመናዊ ባህል ተቋማትና የባህል አመራር ጅማሬና እንቅስቃሴ በተበታተነ ሁኔታ መሰረቱ ቢጣልም ' ለዘርፈ- ብዙው ባህል አውታሮች ተመጋጋቢነት ባለመመቻቸቱ ተገቢው ዘርፉ የእድገት በሚጠበቀው አኳኋን ዕውን ሊሆን አልቻለም፡፡ ይህን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ሕዝቦችና ባህል ከፍተኛ አክብaትና አድናቆት ያላቸው የሀገር ውስጥና አፍሪካውያን ምሁራን ሳይቀሩ ከዘመናዊ የባህል አመራር አኳያ የተለያዩ ፅንሰ ሃሣቦችን በተለያየ ጊዜ ሰንዝረው እንደነበረ የታሪክ ድርሳን ይናገራል፡፡

ለዘርፉ የመጀመሪያ የሆነውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በመስከረም 11 ቀን 1967 ከጽሕፈት ሚኒስቴር / ከግቢ ሚኒስቴር / በተፃፈ አጭር ደብዳቤ' "…የባህል ሚኒስቴር በመቋቋሙ ባህል ነክ የሆኑ መሥሪያ ቤቶች ሁሉ በዚሁ ሚኒስቴር ውስጥ እንዲጠቃለሉ በመወሰኑ…" ከማስታወቂያ“ መርሀ-ብሔር ሚኒስቴር የቴአትርና ሲኒማ ' ከትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር ' የሥነ ጥበብ መምሪያና የአማርኛ መርሃ ልሣን'ከጽሕፈት ሚኒስቴር ብሔራዊና ታሪካዊ ቤተመዛግብት እንዲዛወሩ ሲወሰን&የጥንታዊ ቅርሶች አስተዳደርና ብሔራዊ ቤተ መፃሕፍትና ወመዘክር በዚሁ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እንዲጠቃለሉ ተደረገ፡፡ በመጨረሻም ከሦስት ዓመታት በኋላ የሚኒስቴር መሥሪያቤት 127/69 የባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስቴርን ሥልጣንና ኃላፊነት ሰፋ በማድረግ“ በማጠናከር ሕጋዊ መሰረት ተሰጥቶት በይፋ እዲቀጥል ተደረገ፡፡

Pages: 1  2  3  4