የኢ-ተሳትፎ ፖሊሲ የኢ-ተሳትፎ ፖሊሲ

የኢ-ተሳትፎ ኃላፊነታችን

የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለደንበኞቹ አጥጋቢ፣ ተጠያቂነት ያለበትና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንዲያስችለው ከባለድርሻ አካላት ተገቢውን የግብረ-መልስና ጥቆማ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል፡፡ ባለድርሻ አካላት በዚህ ድረ-ገፅ ላይ በሚገኙት እንደ የውይይት መድረክ፣ የተጠቃሚ አስተያየት መመዘኛ ምርጫዎች፣ ብሎጎች/ጡመሮች እንዲሁም የግብረ-መልስ መሰብሰቢያ ሳጥኖች በመጠቀም ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጋበዛሉ፡፡

 

የግብረ-መልስ አሰባሰብ

ባለድርሻ አካላት በድረ-ገፁ ላይ በሚገኙት የተለያዩ የኢ-ተሳትፎ መገናኛዎች እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ፡፡ ተጠቃሚዎች ሁሉንም የውይይት መደረኮች ያሉትን አስተያየቶችና ፅሁፎች ማንበብ ይችላሉ ነገር ግን አስተያየት መስጠት የሚችሉት የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው፡፡

 

ጠቃሚ ማሳሰቢያ

በዚህ ድረ-ገፅ ላይ በሚፃፉ ማንኛውም አስተየየቶች ሚኒስቴር መ/ቤቱም ሆነ የሚኒስቴር መ/ቤቱን ሠራተኞች ተጠያቂ አያደርግም፡፡