የስብሰባ ማዕከል / የባህል ማዕከል የስብሰባ ማዕከል / የባህል ማዕከል

የኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል አጭር ታሪካዊ ዳራ

የኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል የተባለው ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ህገ መንግሥት ለማርቀቅ የተዋቀረው የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን የተሰሰጠውን ተግባር እንዲያከናውንበት ተብሎ ተቋቋመ፡፡ ህገ መንግሥቱ ከተረቀቀና ከጸደቀ በኋላ ኮሚሽኑ ስራውን ያከናወነበት ድርጅት ቀጣይ ስራ ስላልነበረው፤ የህገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ይገለገልባቸው የነበሩ ንብረቶችን ይዞና “የኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት፤ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆኖ፤ ወደ ህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች እንዲዛወር ተደርጎ በነሐሴ 1988. ራሱን ችሎ ስራውን ጀመረ፡፡

ማዕከሉ ራሱን ችሎ እንዲተዳደር ሲደረግ የሚከተሉትን ተግባራት ያስፈጽማል ተብሎ ታስቦ ነበር፡፡

የኢ... ህገ መንግሥት የተረቀቀበትን፣ የጸደቀበትንና ሥራ ላይ እየዋለ   ያለበትን ሂደት በሥዕል፣ በጽሑፍ፣ በፊልም፣ በኢግዚቢሽን፣ በድራማ፣ በሙዚቃና በመሳሰሉት መልኮች ማዘጋጀት፣ ማደራጀትና ለህዝብ ማሳየት፤

የብሔር ብሔረሰቦችንና ህዝቦችን ግንኙነት የሚያዳብሩ ባህላዊ፣ ሙያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሞያዊ ውይይቶችንና ስብሰባዎችን ማካሄድ፤

የብሔር ብሔረሰሰቦችንና ህዝቦችን ባህላዊ ሙዚቃዎች በማዘጋጀትና በማደራጀት   ለህዝብ ማቅረብ፤

ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዳ ሌሳ ማንኛውንም የንግድ ስራ መስራት፡፡

ማዕከሉ ራሱን ችሎ ሲደራጅ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሠራተኞች ተመድበውለት፤ መጀመሪያ በስራ አመራር ቦርድ ቀጥሎም ከምክር ቤት አባላት በተውጣጣ ኮሚቴ ይተዳደር ነበር፡፡ በኋላም በጊዜያዊነት በተመደበ ስራ አስኪያጅ ሲመራ ቆይቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 23/1990 . ከታህሣሥ 10/1990 . ጀምሮ ተጠሪነቱ ለማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ሆኖ፤ መጠሪያውን እንደያዘ የህግ ሰውነት ያለው ራስን የቻለ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤት ሆኖ ተቋቋመ፡፡ የማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ከከሰመ በኃላ የማዕከሉ ተጠሪነት መጀመሪያ ለወጣቶች ስፖርትና ባህል ሚኒስቴር፤ ቀጥሎም ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሆኖ ስራውን ጀመረ፡፡

ይሁንና የኢትዮጵያ ሰብሰባ ማዕከል ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር አንጻር የጎላ ለውጥ ሊያመጣ ባለመቻሉ የአደረጃጀት ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በዚህም መሠረት በባህልና ቱሪዝም ሚኒሰቴር የመሰረታዊ ለውጥ ጥናት / BPR / መሰረት በብሄራዊ ደረጃ አንድ የባህል ማዕከል ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ጥናቱ በመጠቆሙ የኢትዮጲያ ስብሰባ ማዕከልም የኢትዮጲያ ባህል ማዕከልን ሚና ይዞ በቀድሞ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥናት ሰነድ ውስጥ የተቋቋመው "የባህል ዕሴቶችን ማበልጸግና ለአገልግሎት የማቅረብ ተግባር" እንደ ዋና የስራ ሂደት ተለይቶና ተጠንቶ ስራው እየተሰራ ይገኛል:: በአሁኑ ሰዓት የብሔራዊ ባህል ማዕከሉ ማቋቋሚያ ደንብ ይጸድቃል ተበሎ ይጠበቃል:: በጥናቱ የተመላከቱት የባህል ማዕከሉ ራዕይ ተልዕኮ ¯ላማና ዕሴቶች አንደሚከተለው ቀርቧል:

የስብሰባ ማዕከል / የባህል ማዕከል/ ራዕይ'ተልዕኮ 'ዕሴቶችና ዓላማ

ራዕይ

የባህል እሴቶች መግለጫዎች ብልጽገው፣ተዋውቀውና ለአገልሎት በቅተው ለአገር ልማት ውለው ማየት፡

ተልዕኮ

አገራችን የባህል እሴቶችና መገለጫዎች እንዲበለፅጉ እና ለአገልግሎት እንዲውሉ መሪነት ሚና በመፃወት የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህልበአገር ውስጥና በውጭአገራት በማስተዋወቅ የማዕከሉን ልማታዊ አስተዋፅኦ ማሳደግ፡፡

ዓላማ

ኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላዊ እሴቶች የባህል መገለጫዎችና ሙያዎች አድገውና በልፅገው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኙ ማድረግ፡፡

እሴቶች

  • ባህል የአንድ ሕዝብ በዋጋ የማይተመን ሐበት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
  • በህላዊ እሴቶችን በማበልፀግ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት እንችላለን፡፡
  • ብዝሃ ባህላችን የአንድነት መሰረት ነው፡፡
  • አሳታፊነት ታማኝነት ግልፅነትና ተጠያቂነት የተላበሰ አሰራር ባህላችን ነው፡፡
  • የአገራችንን መልካም ገፅታ መገንባት ተልዕኳችን ነው፡፡