የሰሜን ብሄራዊ የተፈጥሮ ፖርክ

Semien Mountains National Park

የሰሜን ብሔራዊ ፖርክ የሚገኘው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጐንደር ዞን ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢ የተፈጠረ ዝነኛ መሬት ነው፣ የተፈጠረውም በአካባቢው በጐርፍ በተካሄደው የመሬት መሸርሸር ሲሆን በዚህም ምክንያት ውብና ድንቅ የሆኑ ገጸ ምድሮች ተፈጥረዋል፡፡

ወጣ ገባና የሾሉ ጋራዎች ጥልቅ ሸለቆዎችና 15ዐዐ ሜትር ድረስ የሚወርዱ ገደሎች ያሉት ይህ የተፈጥሮ ክልል ከአፍሪካ በከፍታው የታወቀው ራስ ዳሽን ተራራ ይገኝበታል፡፡ ፖርኩ የሰሜን ብሔራዊ የተፈጥሮ ክልል በመባል ይታወቃል፡፡ በተፈጥሮ ክልሉ በጣም ብርቅ የሆነውን ጭላዳ ዝንጀሮ የሰሜን ቀበሮና ዋልያ አይቤክስ በየትኛውም የአለም ክፍል የማይገኙ ብርቅዬ የዱር እንስሳትን የያዘ ቦታ ነው፡፡ የሰሜን ብሔራዊ ፖርክ እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 1978 በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡