6ኛው ጉማ የፊልም ሽልማት ተካሄደ
በአገራችን የፊልም ኢንደስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን በማበረታታት ረገድ ፈር ቀዳጅ የሆነውና በዳይሬክተር በዮናስ ብርሃነ መዋ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ፊልም ሽልማት ለ6ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር በደምቀት ተካሄደ፡፡
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ረመዳን አሸናፊ እንደተናገሩት በሀገራችን ፊልም ኢንዱስትሪ ከተጀመረ ዘመናት ያስቆጠረ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል እድገት አላሳየም ብለው ይህንን እውነታ በመረዳት መንግስት በ2010 ዓ.ም በሀገራችን ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሀገራዊ የፊልም ፖሊሲ መጽደቁን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ፖሊሲ ወደ ተግባር ለመለወጥ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለው ይህ ኢንዱስትሪ በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩትም ይህንን ተቋቁመው በርካታ ፊልሞችን ለማህበረሰቡ እያቀረቡ ህዝባችንን እያስተማሩ እያዝናኑ ለሚገኙ ያለፉትንም ሆነ አሁን በዘርፉ ያሉትን የፊልም ባለሙያዎች ለዚህ ተግባራቸው ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፕሮግራሙ መስራችና ባለቤት የሆነው አርቲስት ዮናስ ብርሃነ መዋ በበኩሉ ፕሮግራሙ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናውን አቅርቦ ጉማ በአህጉራችን የፊልም እንቅስቃሴ ውስጥ ሀገራችንን የሚያስጠራ ዝግጅት የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ በፕሮግራሙም በ18 ዘርፍ የተዘጋጁ ሽልማቶች አሰጣጥ ስነ-ስርዓት የተከናወነ ሲሆን በህይወት ዘርፍ ተሸላሚም አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማው በመሆን ከክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እጅ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
ዜናዎች
- ለመዲናችን ልዩ ድምቀት!
- ኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- የሩሲያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የዲፕሎማና የሜዳልያ ሽልማት ሰጠች፡፡
- ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ፌደሬሽን በባህል፣ በቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ፡፡
- የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሂሩት ካሣው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
- ስፖርት ለሰላም! በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
- ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ አልዶሳሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
- የአዲስዓለም አድባራት ወገዳማት ደብረጽዮን ማርያም ሙዚየም በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ፡፡
- የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ጉባዔ እየተካሄደ ነው
- የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲ ወደ ተግባራዊ እቅስቀሴ ተሸጋገረ፡፡