ዕድሮች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ
በቀጣይ ሶስት ወራትም ወረርሽኙን ለመከላከል ልዩ ዕቅድ አዘጋጅተው ወደስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት ዛሬ ከአዲስ አበባ ዕድሮች ተወካዮች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ የከተማዋ የዕድሮች ምክርቤት ሰብሳቢ አቶ ታምራት ገ/ማርያም እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 6933 ዕድሮች ያሉ ሲሆን ሁሉም ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ የዕድር ስብሰባ ማስቀረታቸውንና በሀዘንና ሌሎች ማሕበራዊ ጉዳዮች ሲኖሩ ውስን ሰዎች ብቻ በጥንቃቄ እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ወቅቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ መረዳዳትን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ዕድሮች በየአካባቢያቸው ላሉ አቅመ ደካሞች ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑንና በሀገር ዓቀፍ ደረጃ መንግስት ወረርሽኙን ለሚያደርገው ርብርብም በጥሬ ገንዘብና በአይነት ድጋፎች እያደረጉ መሆናውን ሰብሳቢው አብራርተዋል፡፡
ባሳለፍነው መጋቢት 29 እና 30 በከተማዋ በአስሩም ክፍለ-ከተሞች ዕድሮች እየተዘዋወሩ ቅስቀሳ ማድረጋቸውንና የዕድር አባላት በማንኛውም እንቅስቃሴያቸው ርቀታቸውንና ንፅህናቸውን በመጠበቅ ራሳቸውን ብሎም ሌላውን ዜጋ ከወረርሽኙ እንዲጠብቁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች እንደሚሰጡ ተናግራዋል፡፡
የሴት ዕድሮች በበኩላቸው በሀዘን ወቅት ከሶስት ያልበለጡ ሴቶች ብቻ እየተቀያየሩ ወደሀዘን ቤቱ እየገቡ በጥንቃቄ ስራቸውን እንደሚሰሩና እንደሚያስተዛዝኑ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ከሴት ዕድር ሰብሳቢዎች የተወከሉት ወ/ሮ ፀሐይ ወዳጆ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለወላጅ አልባ ህፃናትና ለታመሙ የዕድር አባላት ድጋፍ እየተሰበሰበ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
ሌላኛው የውይይቱ ተሳታፊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ መርዕድ ዕድሮች በሀገራችን በሁሉም ቦታ ያሉና በማህበረሰቡ ፍላጎት የተመሰረቱ እንደመሆናቸው ለውጥ ለማምጣትና ተፅዕኖ ለመፍጠር ቀዳሚ ናቸው፡፡ ዕድሮች በሚሰጡት አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማህበራዊ መረዳጃ፣ ማህበራዊ ዋስትናና ማህበራዊ ህክምና መሆን ችለዋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ለመንግስትም ሆነ ለራሱ ለማህረሰቡ ትልቅ ጉልበት ናቸው ብለዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባሕል ዕሴት ልማት ዳይሬክተር ወ/ሮ እስከዳር ግሩም እና የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ወይንሸት ሀይለማርያም በሰጡት ማብራሪያ ውይይቱ የተዘጋጀበት ዋነኛ ምክንያት ዕድሮች ያላቸውን ተቀባይነትና የሚሰሩት ስራ ያለውን ከፍተኛ አቅም በመገንዘብ ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፈተና ለመውጣት በምታደርገው ጥረት ውስጥ ሚናቸውን ለማጠናከር ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ሚኒስቴር መ/ቤታችን ዕድሮች የሚደርጉትን እንቅስቃሴ በመደገፍ ከወረርሽኙም ባለፈ በርካታ ማህበራዊ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ወ/ሮ እስከዳር አረጋግጠዋል፡፡

ዜናዎች
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡
— 10 Items per Page