ዛሬም እንደትላንቱ አኩሪው የመተሳሰብ ባህላችን አብሮን አለ

የሀዋሳ ግራንድ ሞል እና የሃዋሳ ሴንትራል ሆቴል ባለቤት ወይዘሮ አማረች ዘለቀ ያለንበትን አስቸጋሪ ጊዜ በመረዳት ህንፃቸውን ለተከራዮ ነጋዴዎች የሁለት ወር ኪራይ ነፃ አርገዋል። ይህም 1,000,000 ብር ይደርሳል።
ከዚህ በተጨማሪ እኝህ ቅን ኢትዮጵያዊ እናት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ስራ ባይኖርም በሆቴላቸው የሚሰሩ ሰራተኞች ወረርሽኙ አንዳች መፍትሔ እስኪገኝለት ድረስ ከጎናቸው እንደማይለዩ ያረጋገጡ ሲሆን የሀዋሳ ከተማም የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት የ150.000/የአንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
# ግለሰቧ የያንዳንዳችን ሀብት የሁላችን፣ የያንዳንዳችን ችግርም የሁላችን መሆኑን በተግባር አሳይተውናልና ከልብ እናመሰግናለን! #
#የሚሰጡ እጆችን ያብዛልን!#

ዜናዎች ዜናዎች