የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እና የተጠሪ ተቋማቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ናቸው

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እና የተጠሪ ተቋማቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ናቸው
***********

በቅርቡ የቻይናዋን ኦሃን ግዛት መነሻው አድርጎ የተለያዩ ሀገራትን በማካለል ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተለያዩ ተቋማት በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡

በዚህም መሰረት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርና ተጠሪ ተቋማቱ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል በስራ ቦታ ላይ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማሟላትና ሰራተኞችም ሆነ ተገልጋዮች እጃቸውን እንዲታጠቡ ማድረግ፣ የተለያዩ ስብሰባዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንዲካሄዱ ማድረግና የብሄራዊ ሙዚየምና የብሄራዊ ትያትር ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ ይገኝበታል።

ከዚህ በተጨማሪ ከኮሮና በሽታ ምንነት፣ መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማድረስ በተቋማቱ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም የሚገኙ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለህብረተሰቡ የነጻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

በሚኒስቴር /ቤቱና በተጠሪ ተቋማት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ የቅድመ መከላከል ስራዎች እንዲከታተል የተቋቋመው ቡድን በሁሉም ተቋማት ጋር በመገኘት ምልከታ ያደረገ ሲሆን በምልከታውም በእስካሁኑ ሂደት የተከናወኑት ተግባራት አበረታች መሆናቸውንና በቀጣይም በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለባቸው አመላክቷል።

የቫይረሱ ስርጭትን ለመከላከል አለመጨባበጥ፣ ከሚያስሉ፣ ከሚያስነጥሱና ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች መራቅ፣ እጅ ሳይታጠብ ዓይን፣ አፍና አፍንጫ አለመንካት፣እጅን በሳሙና አዘውትረው መታጠብ፣ ሰዎች ወደሚበዙበት ቦታዎች በተለይ የሕመም ስሜት ካለ አለመሄድ፣ በትራስፖርት ላይ፣ ስራ ቦታ እና መኖሪያ ቦታዎች መስኮቶችን መክፈት እንደሚያስፈልግ በጤና ሚኒስቴር መገለጹ ይታወሳል፡፡

 

 

 

 


ዜናዎች ዜናዎች