የጂኦ ስፓሻል መረጃን ለቱሪዝም አገልግሎት ማዋል የሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ፤
ጥቅምት 21/2010 ዓ.ም እያደገ ከመጣው የቱሪዝም ዘርፍ ጋር አብሮ ለመጓዝና በዘርፉ የታቀዱ የልማት ግቦችን ለማሳካት ወቅቱ በሚጠይቀው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚያሥችል የግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ከተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎችና ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሄደ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫውን የሰጡት ከመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /INSA/ በመጡ የጂኦ ስፓሻል ባለሙያዎች ሲሆኑ አጠቃላይ ተቋሙ እያከናወነ ስለሚገኝባቸው የስራ እንቅስቃሴ ገለፃ አድርገው ከባህልና ቱሪዝም ዘርፍ አንፃር ጂኦስፓሻል ምርቶችና አገልግሎቶች ለቱሪዝም ያላቸውን ፋይዳ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የመጀመሪያው ታሪካዊ ቅርሶችን በ3ዲ በማንሳት ሞዴል በማድረግ በዘመናት ሂደት ውስጥ ቅርሶቹ ቢያረጁና ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ በሆነ ሁኔታ ይዘታቸውን ቢለቁ የቀድሞ ማንነታቸውን በጠበቀ መልኩ ለመጠገን የሚያስችል፣ የመስህብ ስፍራዎችና ማዕከል ያደረገ የቱሪስት ካርታ ለማዘጋጀትና የመስህብ ቦታዎችን በምስለ ገፅታ በመያዝ ለጎብኝዎች ግልፅ የሆኑ መረጃዎችን ለመስጠት፣ የመስህብ ስፍራዎችን የይዞታ ካርታ ለማዘጋጀት፣ አዳዲስ የመስህብ ስፍራዎችን ለመለየትና የአካባቢውን የቱሪዝም አቅም በይበልጥ ለመጠቀም የሚያስፈልጉ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለማሟላት እንዲሁም የዱር እንስሳት ቆጠራን ማከናወን እንደሚያስችል በምስል በማስደገፍ አስረድተዋል፡፡
ተሳታፊዎችም በተነሱ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በተለይ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ሁለንተናዊ የሆነ የሀገሪቱን ባህል፣ የቱሪዝም፣ የቅርስና የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማልማትና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ከተቋሙ ጋር በቀጣይ ተቀናጅቶ መስራ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተስማምተዋል፡፡
ዜናዎች
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡