ዜናዎች እና ለውጦች

የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ መስከረም 28/2011 በኢትዮጵያ ጥንታዊ የፅሁፍ ኃብት ያለበትን ሁኔታ የመፈተሽና ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት የመቀየስ ዓላማ ያለው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ጉባዔ በአዲስ አበባ ተከፈተ።

የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲ ወደ ተግባራዊ እቅስቀሴ ተሸጋገረ፡፡

መስከረም 29 ቀን 2011ዓ.ም የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲን ለመተግበር እና የማስፈጸሚያ ስልት ለመንደፍ የተዘጋጀ መድረክ በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ሠላም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ፊልም ፕሮዲውሰሮች ማህበር ትብብር አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ - መዛግብትና ቤተ - መጻሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ተካሄደ፡፡

ከሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር አካባቢ ተፈናቅለው በመጠልያ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ጉብኝት አደረጉ፡፡

መስከረም 25/2011 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በለገጣፎ በጊዜያዊ መጠልያ ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት ”ህፃናትን መንከባከብ ለተሻለ ተስፋ ናህይወት” በሚል መሪ-ሃሳብ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አስጎብኝቷቸዋል፡፡

የመጀመሪያው የኢሬቻ የሰላም ሽልማት ተካሔደ

አዲስ አበባ መስከረም 18/2011 በመጀመሪያው የ’ኢሬቻ የሰላም ሽልማት’ ስምንት ሰዎችና አንድ ቡድን በሰላም ዙሪያ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሽልማት ተበረከተላቸው። የኢትየጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የኢሬቻ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማድረግ መርሃ ግብሩን አዘጋጅተዋል።

በጋምቤላ ክልል ሲካሄድ የነበረው የዓለም ቱሪዝም ቀን በዓል ተጠናቀቀ

የዓለም የቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ ጊዜ በሀንጋሪ (ቡዳፔስት) በአገራችን ደግሞ ለ31ኛ ጊዜ በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልል ዋና ከተማ ጋምቤላና አካባቢዋ ከመስከረም 14/2011 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡