6ኛው የቱሪዝም እና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት መከበር ጀመረ

ከተመሠረተ 49 ዓመቱን ያስቆጠረውና ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራ ረገድ የሚታወቀው የሆቴል እና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ተቋምአዘጋጅነት የተሰናዳው 
ይህ መርሀ ግብር ከግንቦት 5-9/2010 . በተለያዩ መርሀ ግብሮች ይቆያል፡፡

በገነት ሆቴል በተከናወነው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ክብርት / ፎዚያ አሚን እንዳሉት “ተቋሙ ስለዘርፉ በህብረተሰቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠርና ለሀገራችን መለያ የሆነውን የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ይበልጥ ለማስተዋወቅ በተከታታይ አምስትዓመታዊ የቱሪዝም እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት ሲያከብር ቆቷል፡፡ ዘንድሮም “ሰላም ለቱሪዝም፤ ዘላቂ የቱሪዝም ልማት ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል ሲያከብር ለዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃትን የሚፈጥር እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከመሪ ቃሉ ለመረዳት እንደሚቻለው ቱሪዝም ለተያያዝነው የእድገት ጉዞ በዘላቂነት አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባው የሚያመላክት ሲሆን ይህን ሃላፊነት እንዲወጣ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል፡፡

አያይዘውም የሀገራችንን ሰላም በማረጋገጥ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡” ብለዋል፡፡ የተቋሙ ዋናዳይሬክተር አቶ አሸብር ተክሌ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት “የልማት ቁልፉ ኃይል የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ነው፡፡ ሀገራችንም ይህን መሰረት በማድረግ ለትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ትገኛለች፡፡ መንግስትም ቱሪዝም የሚያስገኘውን ማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ፋይዳ በመረዳት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መኖሪያ የበርካታ መስህቦች መገኛ የሆነችው ሀገራችን ከቱሪዝም ዘርፍ የምታገኘውን ሁለንተናዊ ጥቅም አውጥቶ ለመጠቀም ይቻል ዘንድ ከ49 ዓመታ በፊት የተመሰረተው የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጣኛ ተቋም በተለያየ ጊዜ በርካታ ተማሪዎችን እያሰለጠነ ወደ ስራ በማሰማራት ዘርፉ ላይ ትልቅ ስራ አከናውኗል፡፡” ብለዋል፡፡

ለተከታታይ አምስት ቀናት በሚቆየው መርሀ-ግብር ላይ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የህዝብ ተወካዮች /ቤት የባህል ቱሪዝም እና ብዙሀን መገናኛ ጉዳዮች ቋሚኮሚቴ አባላት፣ የፌደራል እና የክልል የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ አመራሮች፣ በግሉ ዘርፍ የተሰማሩ የቱሪዝም ተዋንያኖች፣ ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸውእንግዶች ተገኝተዋል፡፡

 


News and Updates News and Updates