2ኛው የባህልና ቱሪዝም ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ ተካሄደ፡፡

ግንቦት 16/2010 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ  ባህልና  ቱሪዝም ሚኒስቴር፣  በደቡብ // ክልል ባህልና ቱሪዝም  ቢሮ እና  የዋቸሞ  ዩኒቨርሲቲ  በቅንጅት ያዘጋጁት እና  "የጋራ  ባህላዊ  እሴቶች ግንባታ ለዘላቂ  ልማትና  ሰላም!" በሚል  መሪ  ሀሳብ የተዘጋጀው 2ኛው ሀገር አቀፍ የባህልና ቱሪዝም  የጥናትና ምርምር ሀገር አቀፍ  ጉባኤ  በሆሳዕና  ከተማ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።  

 

ጉባኤው በንግግር የከፈቱት የኢ... ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት / ፎዚያ አሚን ኢትዮጵያ ያላት እምቅ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ ሀብትና መስህብ ከሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ልዩ እንደሚያደርጋት በመግለጽ ሀገሪቱ የራሷ የሆነ ባህል፣ እምነት፣ ቋንቋና የአኗኗር ዘይቤ ፊደልና የዘመን አቆጣጠር፣ የሰው ዘር መነሻና የቡና መገኛ ናት ብለዋል፡፡

ይህን ዘርፈ ብዙ የባህል፣ የታሪክና የተፈጥሮ ሀብቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያስገኝ የሚያስችል የባህልና ቱሪዝም ሀብቶችን በዘላቂነት በማጥናትና በማልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጥናትና ምርምር ሊታገዝ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በዘርፉ ያለውን እውቀት ለማዳበር የጥናትና ምርምር ሥራ በመስራት የባህልና ቱሪዝም ሀብቶችን በጥናት እየለዩ ጥቅም ላይ ለማዋል፣ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጥናት በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጦ በመንቀሳቀስ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ጠንካራ ትስስር መፍጠር ያስፈልጋል በማለት አክለዋል፡፡

/ ኤርጎጌ ተስፋዬ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የጥናት፣ ምርምርና ማህበረሰብ አጋርነት /ፕሬዝደንት በበኩላቸው የባህልና ቱሪዝም ስራዎች በጥናትና ምርምር ረገድ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ዩኒቨርስቲው የሚያስተናግደውን የተማሪዎችን ብዝሃነት ለማጠናከርና ለማሳደግ የባህል ዕሴቶቻችንን በምርምር በማዳበር ለህብረተሰቡ ጠቃሚ አገልግሎት ለመስጠት ያግዛልም ብለዋል፡፡

በጉባኤውም ላይ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን ጥናታዊ ጽሁፎቹ የባህላዊ እሴቶችን ጠብቀን በጋራ እያስተሳሰርን ለሰላም ለልማትና ለዲሞክራሲ ግንባታ ማዋል እንዳለብን አመላክተዋል፡፡ እንዲሁም የሰላምን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ አስመልክቶ ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን በተሳታፊዎችም ውይይቶች እየተካሄዱባቸው ይገኛል ፡፡ የጋራ ባህላዊ እሴቶቻችን ላይ ትኩረት ያደረጉ እና  በምሁራን የተጠኑ 15 ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በዕለቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሮች የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል  ባህልና ቱሪዝም  ቢሮ  ኃላፊዎች የአውሮፓ  ህብረት  ተወካዩች፣ ምሁራን፣ታዋቂ  ግለሰቦች፣  እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡


News and Updates News and Updates