የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በመሆን በባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች፤ አገልግሎቶች ገበያ ልማት እና ትስስር ስልቶች የጥናት ላይ የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር መድረክ ከግንቦት 24-25/2010ዓ.ም በደሴ ከተማ ወሎ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በመሆን በባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች፤ አገልግሎቶች ገበያ ልማት እና ትስስር ስልቶች የጥናት ላይ የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር መድረክ ከግንቦት 24-25/2010. በደሴ ከተማ ወሎ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች፤ አገልግሎቶች ገበያ ልማት እና ትስስር ስልቶች በጥናትና ምርምር መታገዝ አለበት፡፡ ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (በወሎ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ ልማትና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ም/ል ፕሬዝዳንት) በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ በባህል ኢንዱስትሪ መስኮች እና አገልግሎቶች የገበያ ልማት ስልቶች በጥናትና ምርምር መታገዝ እዳለበት ገልጸዋል፡፡

ም/ል ፕሬዝደንቷ ይህንን ያሉት በዚህ አውደ ጥናት የዕደ - ጥበብ ውጤቶችን ከማምረትና ከመጠቀም፣ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ፣ በሳይንሳዊ ጥናት ለማስደገፍ እንደዚህ ያለ አውደጥናት መዘጋጀቱ አስፈላጊ ይሆናል ለዚህም የወሎ ዩኒቨርስቲ በባህልና በኪነ- ጥበብ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

ስለሆነም ያሉንን ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ምርቶች ባልተደራጀ ሁኔታ ተበታትነው ከሚመረቱበት ወጥተው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማገዝ በጥናት ተለይተው በብዛት እና በጥራት ለገበያ እና ለቱሪዝም መስህብነት እንዲውሉ በእውቀት ለማስደገፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያስመረቀ የሚያወጣቸው ተመራቂዎች አገር በቀል የዕደ - ጥበብ ውጤቶችን እንደምቹ አጋጣሚ በመውሰድ የሥራ ፈጠራ አካል ለማድረግ የሚያስችል የጥናትና ምርምር ምክረ ሀሳቦች ይወጣሉ፡፡

የጥናትና ምርምሩ መድረክ ዓላማ በባህል ምርቶች፤ አገልግሎቶች ገበያ ልማት እና ትስስር ስልቶች የጥናትና ምርምር ላይ የባህል ኢንዱስትሪ ልማት በሰለጠነ የሠው ኃይል መታገዝ ስላለበት ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተሳሰር ትኩረት ሠጥቶ ለመስራት ነው ሲሉ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማትና ትብብር ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ነጋሽ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ በገበያ ልማት፣ በምርት ጥራት ላይ ተየጀመረውን ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ታስቦ እንደተዘጋጀ አክለው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በባህል ዘርፍ የስራ እድል ፈጠራ፣ ስራውን አስተሳስሮ ከመምራትና ከማስፋፋት አኳያ የሚያጋጥማቸውን ክፍተቶች በጥናት ለይቶ ለመሙላት መሆኑጠቁሟል፡፡

በጥናት መድረኩ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች፣ ከኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ማህበር፣ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር፣ ከኢትዮጵያ ሰዓሊያንና ቀራፂያን ማህበር፣ ከክልሎች ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች፣ ከደሴ ከተማና አካባቢዋ የመጡ ባለሙያዎችና የኪነ - ጥበብ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

 


News and Updates News and Updates