በ2010 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ የባህልና ቱሪዝም ዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ፡፡

በ2010 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ የባህልና ቱሪዝም ዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ፡፡

የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ለሚኒስቴሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በ 2010 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ መስከረም 24 እና 25/2010 ዓ.ም ለተጨማሪ ግብዓት ውይይት አካሄዱ፡፡

ውይይቱ በዘርፍ ተከፍሎ የተከናወነ ሲሆን የባህል ዘርፍ ውይይት ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ልማት  ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ረመዳን አሸናፊ በንግግራቸውም ከባለፈው አፈፃጸማችን መልካም ተሞክሮዎችን ይዘን ድክመታችንን የምናስተካክልበትና ዕቅዳችንን የምናዳብርበት እንዲሁም የ2ዐ1ዐ ዕቅድ በተሻለ መልኩ እንደ ተልዕኮ የተሳካ ለማድረግ ትኩረት የምንሰጠው የምንሰራበት ወቅት ነው ብለዋል፡፡ 

አያይዘውም የመድረኩ ዋና ዓላማ በ2ዐ1ዐ የትግበራ ምዕራፍ ላይ የሚቀሩ ተግባራትን  በተቻለ ውጤት ለመፈፀም ጥሩ አመለካከት ይዘን ለሥራዎቹ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር መልካም አስተዳደር እና ለውጥ ትግበራው ላይ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ለይቶ በማውጣት ውጤት ለማምጣት በጋራ መግባባት እቅዳችንን መፈፀም ይኖርብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የ2ዐዐ9 ዓ.ም. በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና  የ2ዐ1ዐ በጀት ዓመት እቅድ የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ሪፖርት ለተሳታፊዎች ያቀረቡት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእቅድ አፈፃፀም፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰለች ተስፋዬ ሲሆኑ፤ በቀረበው ሪፖርት እና ዕቅድ ላይ ሠራተኞች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች  አቅርበዋል፡፡

በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሚመለከታቸው ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡ ሲሆን አቶ ረመዳን አሸናፊ የበኩላቸውን አስተያየትና አቅጣጫ በመስጠት  ውይይቱን ጠቅልለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የቱሪዝም ዘርፍ ውይይት መድረክን የመሩት የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አሸብር ተክሌ ሲሆኑ የውይይቱን አስፈላጊነት አስመልክቶ እንዳሉት በተያዘው በጀት ዓመት እንደ ዘርፍ በርካታ ተግባራትን እንተገብራለን ብለን ያቀድንበት በተለይ በቱሪዝሙ ዘርፍ የተቀመጡትን ተግባራት ለማሳካት በዘርፉ ያሉ ሰራተኞችና አመራሮች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረው ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ፈጻሚ የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ አመራሩና ሰራተኞች ያነሷቸውን ሀሳቦች በእቅዱ በማካተት ሀገራችን በዘርፉ ለማግኘት ያቀደችውን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስገኘት በትጋት መሰራት እንዳለበት ተናግረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ አመራሮችና ሰራተኞችም እንደተናገሩት እቅዱ ከዝግጅት ምዕራፍ አልፎ ወደ ትግበራ ከመገባቱ በፊት የሚመለከተው አካል መወያየቱ ጥሩ እንደሆነ ተናግረው በተለይ በእቅድ ትስስሩ የክልሎችና የሴክተር መስርያ ቤቶች ተግባራት በግልጽ መቀመጣቸው የሚያበረታታ እና የታቀዱት እቀደው በታለመለት ግዜ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በትጋት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

 


News and Updates News and Updates