በባህልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከተሠማሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር 2ኛው ዓመታዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ፣
"በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት በመምጣት እንዲያለሙ እንዲቀሰቀሱ ጥሪ ቀረበ"
በአገሪቱ ባህልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በውጭ አገር ቆይታቸው ጥረውግረው ያካበቱትን ሀብት፣ ዕውቀትና ልምድ ይዘው ወደ ሀገር ቤት በመምጣት በልማቱ ተሳትፎ በማድረግ እያበረከቱት ያለውን ጥረት ለማጠናከር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የዲያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮችና የዘርፉ ምጣኔ ሀብታዊ አስተዋጽኦ ዙሪያ ግንቦት17/2009 ዓ.ም. ባዘጋጀው ሁለተኛው ዓመታዊ የምክክር መድረክ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ከተሠማሩ የዳያስፖራ ባለሀብቶች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጌትፋም ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡
የምክክር ጉባኤውን በይፋ በመከፈት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ ገ/መድህን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሲሆኑ፣ ባስተላለፉት መልዕክት " አገራችን ለተያያዘችው ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት ግስጋሴ ተሳታፊ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል በውጭ አገርቆይታቸው ወቅት ያፈሩትን ሀብት፣ ዕውቀትና ልምድ ይዘው ወደ ሀገር ቤት በመምጣት ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማስቻል የወጣው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የዳያስፖራ ፖሊሲ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በዘርፉ ተሰማርተው የሚገኙ ከ450 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት እያበረክቱት ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
አክለውም ክብርት ሚኒስትሩዋ በአሁኑ ወቅት ባህልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በአገሪቱ የተፈጠረውን የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ አሁንም ኑሮዋቸውን በውጭ አገር ላደረጉ ጓደኞቻቸውን፣ ዘመዶቻቸውንና ሌሎች የንግድ ሸሪኮች በማስረዳትወደ ሀገር ቤት በመምጣት አንቨስት እንዲያደርጉና ራሳቸውንም አገራቸውንም እንዲጠቅሙ እንዲስቡ፣ እንዲቀሰቅሱ በተጨማሪ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በዕለቱ ሶስት የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች የቀረቡ ሲሆን፤ እነዚህም 1ኛ/ ዳያስፖራው ለአገራችን እያበረከተ ስላለው አስተዋጽኦ እና የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች (በአቶ ሚካኤል ጦቢያስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር)፣ 2ኛ/ የዳያስፖራ ማህበር በኢትዮጵያ (በአቶ አብራሃም ስዩም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር ፕሬዝዳንት)፤3ኛ/ በባህልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት መስክ የዳያስፖራው ተሳትፎ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናት (በአቶ ሙሉነህ ማቴዎስ)፣4ኛ/ በአገራችን የቱሪስት መስህቦች( በአቶ ሲሳይ ጌታቸው ከኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቱሪዝም ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር) ተሳታፊዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው በቅደም ተከል ገለፃዎች ተደርጓል፡፡
ከገለፃዎቹ በኋላ በዘርፉ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው ማነቆ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ካንዳንድ ተሳታፊዎች ተሰብሳቢዎች ጥያቄና አስተያቶች በምረት የቀረቡ ሲሆን፣ ከሕግ ትርጓሜ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ፈልገን አንዳንድ ተቋማትን በምንጠይቅበት ጊዜ እንቅፋት እየተፈጠረብን ይገኛል ብለዋል፡፡
በተለይም በቱር ኦፕሬሽን አንቨስትመንት መስኮች የተቀመጡ የማበረታቻ ስርዓቶች አተገባበር ሰዋዊ እየሆነ በሥራችን ላይ እምነት እንድናጣ እያደረገን ነው፡፡ እነዚህም ከመልካም አስተዳደርና የኪራይ ስብሳቢነት አመለካከት ጋር እንደሚያያዝ በቀረበው ጥናትም የተመላከተ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ በመድረኩ አጽንኦት ተሰጥቶት ውይይቶች ተደርገዋል፡፡
በምክክሩ ከ215 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉ ሲሆኑ፤ እነዚህም ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ ቱሪዝምና የመገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮሚቴ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ ከኢንቨስትምንት ኮሚሽን፣ የዳያስፖራ አባላት፣ ከተለያዩ የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የተጋበዙ የስራ ኃላፊዎች፣ የብሔራዊ ክልሎች የባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተወካዮች፣ የተለያዩ የሕትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተወከሉ ባለሙያዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ መዓዛ ገ/መድህን የዕለቱን ወይይት ሲያጠቃልሉ ያደረግነው ውይይት በጣም ጠቃሚ ሀሳቦችን ያገኘንበት ነው፡፡ የተነሱት ሀሳቦች ለቀጣይ ሥራዎቻችንም ጥሩ ግብዓት እንደሚሆኑ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡፡
የሀገርን ባህል ከመጠበቅ፣ ከማልማትና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ የማድረግ፣ የሀገራችንን ባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች እንዳያድጉ ገበያ እንዳይኖራቸው ገበያ ላይ ጫና እየፈጠሩ ያሉ ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ የታክስና ቀረጥ ጫና በመፍጠር እንዲቀንሱ ማድረግ የኛ ባህላዊ ምርቶች እንዲሸጡ፣ ገበያ እንዲጨምር መደረግ አለበት ለሚለው ተገቢ ነው፡፡ ይህን ለማየት በቅድሚያ ጥናት ማድረግ አለብን ካሉ በኋላ ከሕግ ትርጓሜ ጋር የተያያዙ ብዥታዎችን ለመፍታት በቀጣይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ ከዳያስፖራ ማህበሩና ከሚመለከታቸው የሕግ ተርጓሚ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ተቀናጅተን የምንሠራበት ሁኔታ እንፈጥራለን ሲሉ የጋራ አቅጣጫ በማስያዝ መድረኩ በይፋ ተዘግቷል፡፡
News and Updates
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡