በአንኮበር ወረዳ በጎረቤላ ከተማ ተገንብቶ ለተመረቀው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ሙዚየም የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶች ተበረከቱለት

ጥር 02/2013 ዓ.ም
አንኮበር
ወረዳው ነገስታቱ ይጠቀሙበት የነበሩ በርካታ ታሪካዊ
ቅርሶች ባለቤት ሲሆን እነዚህን ቅርሶች ባሉበት ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ በማሰብ የተገነባው ሙዚየም በርካታ ቅርሶች ወደ ሙዚየሙ እያሰባሰበ የሚገኝ ሲሆን በምርቃቱ ዕለትም በአቶ አዳነ ከተማ ተገኘ ቤተሰቦች የተሰበሰቡ የዳግማዊ ምኒልክ የልጅ ልጅ ይለብሱት የነበረን ካባ እና ከአንድ እንጨት የተሰራ መቀመጫ እንዲሁም ፎቶግራፎችም ለሙዚየሙ ተበርክቷል።
በፕሮግራሙ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመወከል የተገኙት ዶክተር ታደለ ፋንታው እንዳሉት በሀገራችን ታሪክ ትልቅ ቦታ ባለው በዚህ ወረዳ እንዲህ አይነቱ ሙዚየም መገንባቱ አከባቢው ያለውን ቅርስ በአግባቡ እንዲጠብቅ እና ለትውልድ እንዲተላለፍ ትልቅ ፍይዳ አለው ብለው ለጎብኝዎች ክፍት በማድረግ የአከባቢዉ ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለበት ተናግረው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ለሙዚየሙ ቅርሶችን በስጦታ ያበረከቱት እና በዕለቱ "ያልተለበሰው ካባ" የሚለውን መፅሀፍቸውን ያስመረቁት አቶ አዳነ ከተማ እንዳሉት ይህ ሙዚየም በተፈለገው መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለው በዚህ በታሪካዊ ቦታ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተውን ልበ ወለድ መፅሀፋቸውን ማስመረቃቸው በጣም እንደተደሰቱ ተናግረው የተለያዩ ኩነቶችን በታሪካዊ ቦታዎች የማከናወን ባህል ሊዳብር እንደሚገባ ተናግረው ይህንን መፅሀፍ በታሪካዊ ስፍራ እንዲመረቅ ላደረጉ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

News and Updates News and Updates