የኢትዮጵያ ብሄራዊ የባህል ማዕከል የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጣ አይደለም ተባለ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዝያ አሚን እና የባህል ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ ክብርት ብዙነሽ መሰረት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የባህል ማዕከል ሰራተኞችና የአመራር አካለት ጋር የባህል ማዕከሉ እስካሁን ባከናወናቸው ስራዎች፣ በተገኙ ውጤቶች እና በጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በቀን 10/11/10 ዓ.ም  በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርገዋል፡፡በውይይቱን  የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት አዲሱ የባህል ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የባህል ማዕከል ከህዝቦች ባህልና ማንነት ጋር በተያያዘ ትልቅ ተልዕኮ ተሰጥቶት የተቋቋመ ተቋም ቢሆንም እስካሁን ግን የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት አልቻለም ብለዋዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን በበኩላቸው የውይይቱ አላማ እስካሁን በሪፖርት እና በሌሎች አማራጮች የማዕከሉን እንቅስቃሴ በተመለከተ ከተገኘው መረጃ በተጨማሪ የባህል ማዕከሉ ዋና ተዋናይ ከሆኑትን የማዕከሉ ሰራተኞች እና የአስተዳደር አካለት ስለ ማዕከሉ አጠቃላይ አሰራር መረጃ በማግኘት ለቀጣይ ስራ በግብአትነት መጠቀም መሆኑን የገለጹ ሲሆን በተገኘው መረጃ መሰረት ተቋሙ በአገር ደረጃ የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት አንጻር ውስንነት የነበረበት መሆኑን መረዳታቸውንና በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት እና የባህል ልማቱ ላይ በትኩረት በመስራት የባህል ማዕከላት ለኢንደስትሪ ሽግግሩ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ የባህል ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት በተመሳሳይ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ የባህል ማዕከል በስሙ እና በተሠጠው ተልዕኮ ልክ እየሰራ አለመሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ግን ያለንን አጠቃላይ ሀብት አሟጠን በመጠቀም ማዕከሉን በአገር ደረጃ ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 የውይይቱ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው የባህል ማዕከሉ ከባህል ዘርፉ ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎችን ማከናወን እየተቻለ ከአሰራር፣ ከአደረጃጀት እና ከስትራቴጂካዊ አመራር ችግር ጋር በተያያዘ  በሚፈለገው ደረጃ ስራዎችን ማከናወን አለመቻሉን ጠቁመው በቀጣይ ግን በውይይት የተገኙ ሃሳቦችን እና ሚ/ር መ/ቤቱም ሆነ የባህል ማዕከሉ በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት ስራዎችን በማከናወን እና የማዕከሉ ሁለንተናዊ አገራዊ ጥቅም ከፍ በማድረግ የተጀመረውን አዲስ አገራዊ መነሳሳት እና ለውጥ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል፡፡


News and Updates News and Updates