የአብጃታ ሻላ ሃይቆች ብሄራዊ ፓርክን መታደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ፤

ካሉን ብሄራዊ ፓርኮች በጉዳት ከሚታወቁት አንዱ ነው። የአብጃታ ሀይቅ በገባሮቹ ችግር ፣የዝዋይ ሀይቅ መቀነስ ፣በአካባቢው ያለው የሶዳ አሽ ፋብሪካ ፣የህገ ወጥ አሸዋ ማውጣት ፣የግራር እንጨት ለከሰል መዋል ወዘተ ችግሮች ሆነው ፓርኩ ጉዳት ላይ ወድቋል ሀይቁም በመቀነስ ላይ ነው። በአስቸኳይ መታደግ ካልተቻለ ፓርኩም ይጠፋል ሃይቁም በ15 አመት ጊዜ ሊደርቅ እንደሚችል ጥናቶች እንደሚያሳዩ በክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን የተመራ የአመራሮች ቡድን በሻሸመኔ ከተማ ምእራብ አርሲ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ባደረጉት ውይይት ወቅት ተገልጿል። ፓርኩ ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብት ስለሆነ በቀላሉ መታደግ የሚቻል በመሆኑ ህዝብን በማወያየትና ዘላቂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ አማራጮችን በማፈላለግ በጋራ መፍታት እንደሚገባ ለዚህም ከፌደራል እስከ ወረዳ ያለን ሁላችንም የየበኩላችንን መወጣትና ተግባራትን በፍጥነት ማከናወን እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ይህ የአመራር ቡድን በፓርኩ በመገኘት ገብኝት በማድረግ ያለበትን ሁኔታ ይመለከታል። ፓርኩ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥም ሆኖ በዚህ አመት 13000 የውጭ ቱሪስቶች ጎብኝተውታል። ታዲያ ከተጋረጠበት የመጥፋት አደጋ ብንታደገው ምን ያህል ተጠቃሚ መሆን ይቻል ነበር? ክልሉ ዞኑና ወረዳው አይናቸውንና ሙሉ ትኩረታቸውን ሊሰጡት ይገባል!!!


News and Updates News and Updates