ሀገር አቀፍ የስርአተ ጽህፈት ጉባኤ ተካሄደ !

 የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር ያዘገጀው አገር አቀፍ የስርዓተ ጽህፈት ጉባኤ ግንቦት 23/2010 ዓ.ም በጌት ፋም ሆቴል ሲያካሂድ  በጉባኤው ላይ ከክልል  የባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ በአገር ውስጥ ካሉ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የተወጣጡ የዘርፉ  ምሁራን፣ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ  እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

 

በጉባኤው  የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከስርዓተ ጽህፈት ማበልጸግና መጠቀም ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ  ሀሳቦች ላይ ትኩረት ያደረጉ  ጥናታዊ ጽሁፎች በዘርፉ ምሁራን ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል ፡፡ The Oromo alphabet in LAGIM በአቶ አበበ ቀኖ፣ The Ethiopian writing system and its contributions to Ethiopian nationhood በዶ/ር አየለ በክሪ፣ የኽምጣጋ ቋንቋ የስርዓተ ጽህፈት ቅኝት የፊደል ገበታ ዝግጅት በዶ/ር ሸጋው ወዳጅ እና በ ዶ/ር መለሰ ገላነህ፣     ለኦሮሚኛ ስርአተ ጽህፈት ላቲን ወይስ ፊደል በአቶ ዝናወርቅ አሰፋ  ከቀርቡት ጥናታዊ ጽሁፎች መካከል ይገኙበታል፡፡

በመጨረሻም ተሳታዎች ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያት እንደዚህ አይነት በጥናት ላይ ተመስርተው የሚቀርቡ ጽሁፎች በቀጣይ በተለያዩ ሀገሪቷ ውስጥ ባሉ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ለሚደረጉ ጽሁፎችና የፊደል ገበታ ዝግጅቶች  ከፍተኛ አስተዋጽኦ አስተያየታቸውን እንደሚያደርጉ አስተያየታቸውን  ገልጸዋል፡


News and Updates News and Updates