ለፌዴራል የግለሰብ አስጎበኚዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንምባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ፤

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለፌዴራል ግለሰብ አስጎበኚዎች በጌትፋም ሆቴል ለሰባት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሚያዚያ 21/2010ዓ.ም ጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው በዋናነት ሠልጣኞች በግለሰብ አስጎበኚነት ሙያቸው ያላቸውን  ዕውቀትና ክህሎት በማሻሻል ወደ ላቀ ደረጃ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ለማስቻል ሲሆን፣ በተለይ የሀገሪቱን ባህልና ታሪክ በአግባቡ አውቀው ለቱሪስቱ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት እንዲያስተዋውቁ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርላቸው ነው፡፡

ሠልጣኞች የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ምን ምን መደረግ አለበት በሚል ለቀረበላቸው የመወያያሳ ሀሳብ በመነሳት ለቱሪዝም ዘርፉ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ተሳስሮ መስራት እንደሚጠበቅባቸው በመግለጽ፣ መደረግ ይገባል ያሏቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ በተለይ በቱሪዝም ትምህርት ዘርፍ ተመርቀው የሚወጡ ወጣት ተማሪዎች ወደ ዘርፉ ሥራዎች እንዲገቡ የሚያስላቸው ዕድል በጣም የጠበበ በመሆኑ በሀገሪቱ የተሠማሩ የቱር ኦፕሬሽኖች ካምፓኒዎች ያለው ቸለልተኝነትና ከገበያ ላይ የባለሙያ ቅጥር ከመፈጸም ይልቅ በቤተሰቦችና ዘመዶች እንዲሸፈኑ የሚያደርጉበት ሁኔታ በብዛት ስላለ፤ ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት መነጋገርና መልክ ማስያዝ ይገባል፤ የቱር ኦፕሬሽን ሥራ በቱሪዝም ሙያ በተማረ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ የበለጠ ለዘርፉ ልማት የሚያግዘን ነው ሲሉ  የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች አንስተዋል፡፡

በአወያዮችም በሠልጣኖች በተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ላይ  ማብራሪያዎች የተሰጠ ሲሆን፣  የቱሪዝም ኢንዱስትሪው በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ጥቅም እንዲያስገኝና የዘርፉም አገልግሎቶች በተሻለ የሰው ኃይል እንዲመራ ለማድረግ በመንግስትም  ሆነ በባለድርሻ አካላት መከናወን የሚገባቸው ሥራዎች በዋነኛነት  ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሚሠሩ፤ በተለይም ዘርፉ ላይ የተሠማራው እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ለቱሪዝም ልማት የሚኖረው ሚና እንዳለ ሆኖ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ተሳስሮ መሥራት እንደሚገባውና ይህንን ለማስኬድ አላሰራ ያለም የአሠራር ደንቦችን /መስፈርቶች/ ለማሻሻል ያስጠናውን ሰነድ ለመንግስት ም/ቤት መላኩን፣ አሁንም ቢሆን ለዘርፉ ልማት የሚጠቅሙና ክፍተት ያለባቸው ሕጎች ካሉ በቀጣይም በምናዘጋጃቸው የጋራ መድረኮች እየተለየ የሚሠሩ መሆኑን፣ ከዘርፉ ባለሙያ ጋር ተሳስሮ ለመስራት ጥያቄዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚቻለው በቡድን ተደራጅቶ ለመምጣት ማህበር መመስረት አንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡ እንደዚሁ የዘርፉ አንቨስትመንት በተማረ የሰው ኃይል እንዲመራ በሚለው ወደ ዘርፉ ለመቀላቀል ዕድል የገጠማቸው በርካቶች ቢኖሩም የመነሻ ካፒታል እጥረት የገጠማቸው መኖሩንና የቱሪዝም ልማት የሚረጋገጠው ደግሞ በተማረ ሰው ኃይል ሲመራ መሆኑንና ለዘርፉ ትክክለኛ ዕውቀት ያለው ሰው አሁንም እንደሚያስፈልግ፣ ሕጋዊ መታወቂያና ባጅ አሰጣጥ መስፈርትና ሥነ ምግባር ጋር ተያይዞ የቱሪስቱ አገልግሎት ሰጪ አስጎበኚ ባለሙያዎች ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ከክልሎች ጋር በቅንጅት የሚሠራበት አሠራር መዘርጋቱ በተጨማሪ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም ሠልጣኞች በተሰጣቸው ሥልጠና የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስቻላቸው መሆኑን በማረጋገጥ እንዲህ ዓይነት ሥልጠና እንድናገኝ  በማድረጋችሁ በሚኒስቴር  መስሪያ ቤቱ ስም ምስጋና ይገባቸዋል” ብለዋል፡፡ ከዚያም ለሠልጣኞች የምስክር ወረቀት  አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት በሚኒስቴሩ የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ  በአቶ ስለሺ ግርማ ተከናውኖ መርሐግብሩ በይፋ ተዘግቷል፡፡

 

 

 

 

 


News and Updates News and Updates