፲፪ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሰመራ ከተማ ተከበረ፡፡
፲፪ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሰመራ ከተማ ተከበረ፡፡
የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት የፀደቀበትን ፳፫ኛ ዓመት እና የብሔር ብሔረ-ሰቦች ቀን ፲፪ኛ ዓመት በዓል አከባበር በህገ-መንግሥታችን የደመቀ ህብረ-ብሔራዊነታችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል ከህዳር ፳፮ እስከ ፳፱/ ፪፼፲ በልማታዊ ኤግዚቢሽን፣ በንግድና ባዛር በሲምፖዚየም፣ እንዲሁም በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ በክልሉ መዲና ሰመራ ከተማ ተከብሯል፡፡
ለዚህ ታላቅ በዓል ሰፊ ዝግጅት በማድረግ እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ህዝቡ ለመላው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ህዝቦች ያለውን ክብርና ፍቅር ወገናዊነቱን በግልፅ ያሳየበት ነበር፡፡
የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች በህገ-መንግስቱ አማካኝነት የተጎናጸፏቸውን ድሎች እውን ከሚያደርጉባቸው አደረጃጀቶች መካከል ከግንባር ቀደሞቹ ተርታ ተጠቃሽ በመሆኑ በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚከናወኑ የማስተዋወቂያ ሥራዎች ላይ የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን መልካም ገጽታ በመገንባት ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን ሁኔታዎች መፍጠር ላይ በማተኮር የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
በዚህም ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች በተከበሩ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ተሳትፎ በማድረግ ተልዕኮውን ለመወጣት የተንቀሳቀሰ ሲሆን ዘንድሮም በአፋር ብሔራዊ ክልል በሰመራ ከተማ በድምቀት በተከበረው በዓል አካል በነበረው የልማት ኤግዚቢሽን ላይ የሚኒስቴር መ/ቤት ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴን በማካተት አጠቃላይ የዘርፉን እንቅስቃሴ ሊያሳይ በሚችል መልኩ ከፍተኛ የሆነ የማስተዋወቅ ስራ አከናውኗል፡፡
News and Updates
- የገዳ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የተካሄደው ዝግጅት ተጠናቀቀ
- የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ
- ቱሪዝም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የማስተዋወቅ ስልጠና ሰጠ፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰርከስ ጥምረት ተመሰረተ
- የጎብኝዎች የደህንነት መጠበቂያ ፕሮቶኮል በተመለከተ ለሼፍ ማህበራት ስልጠና ተሰጠ።
- በሀገራችን የመጀመሪያው የማደጎ ዛፍ ተከላ ፕሮጀክት በላሊበላ ተጀመረ
- በአይነቱ ልዩ የሆነ የእጽዋት ዓለም ፕሮጀክት በቅዱስ ላሊበላ የቱሪስት መዳረሻ ይፋ ሆነ፡፡
- የብርቅዬ ባህላዊ የመድኃኒት ዕጽዋት ችግኞች ተከላ ተካሄደ፡፡
- የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
- ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም አጀንዳ!!›› በሚል የተዘጋጀው የቀጣይ አስር ዓመቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕቅድ ለፌደራል ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡