የክስታንኛ-አማርኛ-እንግሊዘኛ ልሳነ-ሳልስ መዝገበ ቃላት ተመረቀ

ክስታንኛ-አማርኛ-እንግሊዘኛ ልሳነ-ሳልስ መዝገበ ቃላት ተመረቀ

 

የጉራጌ ክስታኔ ክስታንኛ-አማርኛ-እንግሊዘኛ ልሳነ-ሳልስ መዝገበ ቃላት ለክስታንኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ በክስታንኛ ቋንቋ መማር ለሚሹና በቋንቋው ጥናትና ምርምር ለሚያካሂዱ ተመራማሪዎች እንዲያገለግል ሆኖ በዓይነቱ ለየት ባለ መልኩ ከ700 በላይ ቃላትን የያዘውና በአዘገጃጀቱ የተደነቀለት የክስታንኛ-አማርኛ-እንግሊዘኛ ልሳነ-ሳልስ መዝገበ ቃላት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እሁድ ታህሣሥ 1/2010 ዓ.ም. የዞኑ ተወላጆችና የተለያዩ የትምህርት ተቋማትና የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሥነሥርዓት ተመረቀ፡፡

መዝገበ ቃላቱን በጋራ ያዘጋጁት የጉራጌ ክስታኔ ሕዝብ ልማት ማህበር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር ሲሆን፣ የልማት ማህበሩ ከሚያደርገው የአካባቢ ልማት እንቅቃሴ በተጨማሪ የማህበረሰቡን ቋንቋ ማሳደግ ባሻገር ለቀጣይ ጥናትና ምርምር ሥራ እንዲያግዝ ለሕትመት ያበቃው መዝገበ ቃላት ለቋንቋው ልማትና በቋንቋው መማር ለሚሹ እንደማጣቀሻ በመሆን እንደሚያገለግል ሆ በመሰናዳቱ ፋይዳው ቀላል ግምት የሚሰጠው እንዳልሆነ በማስገንዘብ በምረቃው ሥነሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም ለአዘጋጆቹ ምስጋናና መልዕክት በማስተላለፍ፤ መርቀው ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡

 

News and Updates News and Updates